የኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ የኢኮኖሚ ሕግጋት ቅኝት፦ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና የግልግል ዳኝነት

Authors

  • ዘውድነህ በየነ ኃይሌ
  • ዎን ኪዳኔ

Abstract

ይህ ጽሑፍ የኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ የኢኮኖሚ ሕጎችን በተለይም ንግድን፥ ኢንቨስትመንትንና የግልግል ዳኝነትን የሚመለከቱትን ሕጎች እድገቶችንና አሁን ያሉበት ሁኔታን በጥልቀት ይመረምራል። እነዚህ የሕግ እድገቶች ግልፅ ባልሆነ ምክንያት አስቀድመው ይሁንታን ካገኙ የሕግ ሰነዶች የተለዩ መሆናቸውን በግኝቱ የዳሰሰው ይህ መጣጥፍ፤ ተቀባይነት ያለው፥ ምክንያታዊ፥ ሊረጋገጥ የሚችል እና ለሙግት የሚመች ኢኮኖሚያዊ፥ ማህበራዊና ሌሎች ዓላማዎችን ለማሳካት ሲባል ልዩነቶችን መቀነስ እንደሚገባ ምክረሀሳብ ይሰጣል።

Downloads

Published

2025-09-14