የአሌ ቋንቋ ሥርዓተ ድምጽና ሥርዓተ ጽሕፈት

Authors

  • ዮናስ በቀለ
  • ሀረገወይን ከበደ

Keywords:

የአሌ ቋንቋ፣ ሥርዓተ ድምፅ፣ ሥርዓተ ጽሕፈት፣ አሌ ዞን፣ ደቡብ ኢትዮጵያ

Abstract

ይህ ጥናት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚነገረውና የኩሺቲክ ቋንቋ ቤተሰብ አባል የሆነው የአሌ ቋንቋን
የድምፅ ሥርዓት መመርመር እና ለቋንቋው ተስማሚ የሆነ ሥርዓተ ጽሕፈት መቅረጽ ላይ ትኩረቱን
አድርጓል። ጥናቱ በቋንቋው ውስጥ ያሉትን ተነባቢ ድምፆችንና አናባቢ ድምፆችን ጨምሮ የቋንቋዉን
ባሕሪ እና የድምፅ ቆጠራ አጠቃላይ መግለጫ ለመስጠት ያለመ ነው። በተጨማሪም እነዚህን ድምፆች
ለመወከል የሚያገለግሉትን የአጻጻፍ ሥርዓት ስምምነቶችን ጥናቱ አቅርቧል። በድምጽ ሥርዓቱ እና
ሥርዓተ ጽሕፈት መካከል ያለውን ግንኙነት መርምሯል። መረጃ የተሰበሰበው የስዋዴሽ የቃላት ዝርዝር
በመጠቀም በቃለ መጠይቅ፣ በጽሑፍ መጠይቅ እና በአፍ መፍቻ ቋንቋ ተናጋሪዎች ምልከታ ነው።
ትንታኔው የሚያተኩረው የአሌ ስነ-ድምጽና ስርዓተ-ድምጽ አሐዶችን በመለየት እንዲሁም ውክልናቸውን
የሚቆጣጠሩትን የአጻጻፍ መርሆችን በመመርመር ላይ ትኩረት አድርጓል። የጥናቱ ግኝቶች ስለአሌ ቋንቋ
ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ከመስጠቱም ባሻገር ለወደፊት ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ምርምር ማድረግ ለሚፈልጉ
ምሁራን ሁሉ ጠቃሚ መረጃ ይሰጣቸዋል ተብሎ ይታመናል። እንዲሁም የቋንቋው ተናጋሪ የሆነው የአሌ
ሕዝብን ለማስተዋወቅ ተጨማሪ መረጃ እና ግንዛቤ እንዲፈጠር አስተዋጽኦ ያደርጋል። ጥናቱ የአሌ ቋንቋ
የድምፅ ሥርዓቱ ዝርዝር መግለጫ በመስጠት 32 ተነባቢ ድምፆች እና አምስት አናባቢ ድምፆች ጥናቱ
ለይቷል። የተነባቢ ድምፆች መጥበቅና መላላት የትርጉም ለውጥ እንደሚያመጡና እንደዚሁ የአናባቢዎች
መርዘምና ማጠር የትርጉም ለውጥ እንደሚያመጡ በጥናቱ ተመላክቷል። በመጨረሻም፣ የተሻለ
አገልግሎት ሊሰጥ የሚችለውን ሥርዓተ ጽሕፈት ለቋንቋው ተዘጋጅቷል።

Published

2026-08-14

How to Cite

በቀለ ዮ. ., & ከበደ ሀ. . (2026). የአሌ ቋንቋ ሥርዓተ ድምጽና ሥርዓተ ጽሕፈት. ZENA-LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures), 35(1), 162–182. Retrieved from https://ejol.aau.edu.et/index.php/JAELC/article/view/13992