የግብረ ገብ ሐሳቦች በበዓሉ ግርማ ‹‹የህሊና ደወል››

Authors

  • ደሳለኝ ሥዩም (ዶ/ር)

Keywords:

[ፍልስፍና፣ ግብረ ገብ፣ መስዋዕትነት፣ የህሊና ደወል

Abstract

ይህ ጥናት ከበዓሉ ግርማ ልቦለዳዊ ሥራዎች አንዱ የሆነውን ‹‹የህሊና ደወል›› እንደገና ያነባል፤ እንደገና
ይፈክራል። የአጥኝው የንባብ ቅኝትም የግብረ ገብ ፍልስፍና ጽንሰ ሐሳቦችን ያማከለ ነው። በተደረገው
ቅድመ ጥናት የንባብ ጥረት የህሊና ደወልን ከግብረ ገብ ፍልስፍና አንጻር የተነተነ አጥኝ አለመገኘቱ የዚህ
ጥናት አነሳሽ ሰበብ ሆኗል። በመሆኑም ጥናቱ ከዚህ በፊት በሌሎች አጥኝዎች ያልታዬ እይታን ስለመያዙ
አጥኝው ያምናል። ይህ ጥናት ዓይነታዊ የጥናት ዘዴን የተከተለ በባህል ጥናቶች (Cultural Studies)
የጥናት ንድፈ ሐሳብ የተቃኘና ትኩረቱም የነገረ ግብረ ገብ (Morality) ሐተታና ፍካሬ ነው። ጥናቱ
በዋነኝነት ደራሲው በ‹‹የህሊና ደወል›› ውስጥ ያነሳቸውን የግብረ ገብ ፈተናዎችና የተጠቀመባቸውን
የማርገቢያ ፈሮች ከመሰዋእትነት ምግባራዊ ፍልስፍና (Altruistic morality) ጽንሰ ሐሳብ አንጻር
ይተነትናል። በጥናቱ ለመገንዘብ እንደተቻለው የህሊና ደወል ሦስት አንብሮዎችን (Thesis) እንደ መንገድ
(Routes) በማበጀት የጠራ የግብረ ገብ ፍልስፍናን ያራምዳል። የመጀመሪያው አንብሮ መስዋዕትነት፣
ሁለተኛው ‹‹የፍቅር መሰላሉ ዕውቀት ነው›› ሦስተኛው ደግሞ አንድን ተግባር በተገቢው ሰዓት መከወን
(ሥራ በጊዜ) የሚሉ መሆናቸው ለማዬት ተችሏል። ይህ የግብረ ገብ ፍልስፍናም በጥቂቶች መስዋዕትነት
የብዙኃን ደስታ ለመፍጠር የሚመኘው የመስዋዕትነት ምግባራዊ ፍልስፍና (Altruistic morality)
ተመሳስሎሽ መሆኑ ታይቷል።

Published

2026-08-14

How to Cite

ሥዩም (ዶ/ር) ደ. (2026). የግብረ ገብ ሐሳቦች በበዓሉ ግርማ ‹‹የህሊና ደወል››. ZENA-LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures), 35(1), 1–21. Retrieved from https://ejol.aau.edu.et/index.php/JAELC/article/view/13987