የነውር እሳቤ በሰሜን አቸፈር ማኅበረሰብ የዕደጥበባት ዝግጅትና አጠቃቀም ዐውድ ውስጥ

Authors

  • ሙሉፀሐይ ገነት
  • የኔዓለም አረዶ
  • ዓለሙ ካሣዬ

Keywords:

[ነውር፣ ዕደጥበባት፣ ሰሜን አቸፈር፣ ዐውድ]

Abstract

ጥናቱ በዕደጥበባት ዝግጅትና አጠቃቀም ዐውድ ውስጥ የማኅበረሰቡን የነውር እሳቤ መተንተንን አላማው ያደረገ ሲሆን ዓይነታዊ የምርምር ዘዴን የተከተለ ነው። በሰሜን አቸፈር ወረዳ ከሚገኙ ሠላሳ ኹለት ቀበሌዎች መካከል በዓላማተኮር ንሞና ስምንት ቀበሌዎችን በመምረጥ በተሳትፏዊና ተዓቅቧዊ ምልከታ፣ በከፊል ነጻና በነጻ ቃለመጠይቅ እንዲሁም በቡድን ተኮር ውይይት መረጃዎች ተሰብስበዋል። መረጃዎቹ በማኅበራዊ ግንባታና በመዋቅራዊ ጠቀሜታዊነት ንድፈሃሳቦች ተቃኝተው ተተንትነዋል። ከግኝቱም በማኅበረሰቡ የዕደጥበባት ዝግጅትና አጠቃቀም ዐውድ ውስጥ የሚስተዋሉ የነውር እሳቤዎች መነሻቸው የማኅበረሰቡ ልማዳዊ እምነቶች እንደሆኑ ከመረጃዎች ታውቋል። ይኸም ማኅበረሰቡ ነውሮችን በመጠበቁ አገኛለሁ ብሎ ከሚያምነውና በአንጻሩ በመጣሱ ደግሞ ይደርስብኛል ብሎ ከሚያምነው ነገር አንጻር የሚታዩ ናቸው። በዕደጥበባቱ አዘገጃጀትና አጠቃቀም ዐውድ ውስጥ ከክብር ጋር የተያያዙ፣ ከበረከትና ከገድ ጋር የተያያዙ እንዲሁም ከክፉ ዐይን ተጋላጭነት ጋር የተያያዙ የነውር እሳቤዎች እንዳሉ መረጃዎች አመላክተዋል። በተጨማሪም በማኅበረሰቡ እምነት መሠረት ነውሮች ለተጠኚው ማኅበረሰብ ማኅበራዊና ሥነልቦናዊ መረጋጋት የመፍጠርና መዋቅራዊ ሥሪትን የማጽናት ሚና እንዳላቸው ይታመናል። በአንጻሩ ማኅበረሰቡ ነውር ብሎ ያወጃቸውን ክልከላዎች መጣስ ማኅበረ ባህላዊ ቅጣት የሚያስከትል ሲሆን ቅጣቱም ከክብር መውረድ፣ ትችት፣ ለመጥፎ ነገሮች ተላልፎ መሰጠት፣ የትዳር ፍቺና የማዕረግ ወይም የሹመት መነጠቅ የሚያስከትል እንደሆነ ጥናቱ አሳይቷል።

Published

2025-09-29

How to Cite

ገነት ሙ. ., አረዶ የ. ., & ካሣዬ ዓ. . (2025). የነውር እሳቤ በሰሜን አቸፈር ማኅበረሰብ የዕደጥበባት ዝግጅትና አጠቃቀም ዐውድ ውስጥ. ZENA-LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures), 34(2). Retrieved from https://ejol.aau.edu.et/index.php/JAELC/article/view/12680