በአማርኛ መማሪያ መፃህፍት ውስጥ የቀረቡ የሰዋስው ይዘቶች ሰዋስዋዊነት

Authors

  • ጌታሁን አማረ

Keywords:

ቁልፍ ቃላት፦ [ሰዋስዋዊነት፣ታህታይ፣ ላዕላይ፣ አፍ-ፈት፣ካልዓይ፣ ኑረት]

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በተለያዩ ክልሎች በ7ኛና በ8ኛ ክፍል አማርኛን እንደአፍ መፍቻና እንደሁለተኛ ቋንቋ ለሚማሩ ተማሪዎችና ለሁለተኛ ደረጃ (9ኛና 10ኛ ክፍል) ተማሪዎች ተዘጋጅተው በ2015 ዓ.ም. በስራ ላይ በዋሉ የአማርኛ መማሪያ መፃህፍት ውስጥ የቀረቡ የሰዋስው ይዘቶችን ከቋንቋው ሰዋስዋዊ ባህሪያት አንፃር ሰዋስዋዊነታቸውን መገምገም ነው። የጥናቱ መረጃዎች የተሰበሰቡት በክልሎች፣ በከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎችና በትምህርት ሚኒስቴር ለተጠቀሱት የከፍል ደረጃዎች ከተዘጋጁት መማሪያ መፃህፍትና የመምህር መምሪያ ነው። በመማሪያ መፃህፍቱ የቀረቡት የሰዋስው ይዘቶች ‘ማስታወሻ’ በሚል ንኡስ ርዕስ ስር በቀረቡ ማብራሪያዎች፣ በምሳሌዎች፣ በመልመጃዎችና በመምህር መምሪያ ውስጥ በቀረቡ የመልመጃዎች መልሶች ነው። መረጃዎቹ የተተነተኑት በገላጭ የምርምር ዘዴ ሲሆን፣ ትንታኔውም ይዘቶቹን በምዕላድ፣ በሀረግና በአረፍተነገር ክፍሎች በመመደብ ቀርቧል። የሰዋስው ይዘቶቹ በአብዛኛው የቋንቋውን ስርዓት ጠብቀው የቀረቡ ሲሆኑ የተወሰኑ ይዘቶች ግን የቋንቋውን ሰዋስዋዊ ባህሪ ያልጠበቁና የቋንቋውን ሰዋስዋዊ ባህሪ ያጡ ሆነው ተገኝተዋል። ለወደፊት መማሪያ መፃህፍቱን ለማሻሻ ይረዳ ዘንድ ጥናቱ ያተኮረውም በችግሮቹ ላይ ነው። ከታዩት ችግሮች ተዘውትረው የታዩት ስነምዕላዳዊ ይዘቶች ናቸው። ሐረግ ነክ ከሆኑት ውስጥ ተውሳከ ግሳዊና መስተዋድዳዊ ሐረጎች ቀላል የማይባል ችግር ታይቶባቸዋል። በአረፍተነገር ደግሞ የፅንሰ ሀሳብም የመዋቅርም ችግር ታይቷል። የመዋቅር ችግሮቹ በቋንቋው ለየት ያለ መዋቅራዊ ባህሪ ያለውን የኑረት ግስን መዋቅራዊ ባህሪ በተመለከተ ክፍተት እንዳለ መረጃዎቹ አሳይተዋል።

Published

2025-07-08

How to Cite

አማረ ጌ. . (2025). በአማርኛ መማሪያ መፃህፍት ውስጥ የቀረቡ የሰዋስው ይዘቶች ሰዋስዋዊነት. ZENA-LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures), 34(1). Retrieved from https://ejol.aau.edu.et/index.php/JAELC/article/view/12024