የጀግና ብያኔ በለቅሶ ዐውድ ላይ በሚከወን የፉከራ ቃል ግጥም ክዋኔና ይዘት ውስጥ በባህር ዳር ከተማ፣ በሰባታሚት ቀበሌ ማሳያነት

Authors

  • አስቴር ሙሉ

Keywords:

ቁልፍ ቃላት፡- [ጀግና፣ፉከራ፣ቃል፤ግጥም፣ክዋኔ]

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በባህር ዳር ከተማ፣ በሰባታሚት ቀበሌ ለቅሶን አጋጣሚ አድርገው በሚከወኑ ቃል ግጥሞች ክዋኔና ይዘት ውስጥ የጀግናን ብያኔ መመርመር ነው። ጥናቱ በለቅሶው ዐውድ ውስጥ የፉከራ ቃል ግጥሞችን ክዋኔ ማሳየት፣ የጀግና መገለጫ እሴቶችን መለየት፣ በግጥሞች የተገለፀውን የጀግና ብያኔ ማሳየት የሚሉ ዝርዝር ዓላማዎች አሉት። ጥናቱ ዓይነታዊ ሲሆን መረጃዎች በምልከታና በቃለ መጠይቅ ተሰብስበውና የምርምር ጥያቄዎችን ከመመለስ አንፃር ተመድበው፣ በክዋኔያዊና ተግባራዊ ንድፈ ሃሳቦች ተተንትነዋል። የመረጃ ትንተና ውጤቱ እንደሚያሳየው የፉከራው ክዋኔ መግቢያ፣ ጊዜ ክወና (ሀተታ) እና መዝጊያ የሚል የታወቀ ቅርፅ አለው። በፉከራው ውስጥ የከዋኝን ሚና የሚጫወቱና ፉከራው የሚከወንበትን ፋይዳ የሚያጎሉ፣ በአንደኛና በሦስተኛ መደብ የቀረቡ ሁለት የትረካ አንፃሮች አሉ። ለቅሶን መሠረት አድርገው የሚከወኑ ፉከራዎች መሠረታዊ ትኩረታቸው ሟች በሕይወት እያለ የነበረውን ስብዕና መግለፅ ቢሆንም አልፎ አልፎ የሟችን ማንነት ከመግለፅ አንፃር ሥራዬ ተብሎ የሚደረግ ግነት አለባቸው። በሥነቃሉ የቀረበው የሟች አካላዊና መንፈሳዊ ማንነት ሙሉ በሙሉ የግለሰቡ መልክ አይደለም። ይልቁንስ ማኅበረሰቡ ባበጀው ባህል ውስጥ መገለጫ የሆኑ እሴቶች ትርጓሜ ነው። ጀግና የማኅበረሰቡን እሴትና ደንብ ማክበርና መጠበቅ የቻለ፣ማኅበረሰቡ የተጠየፋቸውን ባህርያት የተጠየፈና ለማስወገድ የሚሠራ ሰው መሆኑን የሚጠቁሙ ውጤቶች ተገኝተዋል። ከውጤቶች በመነሳት በከዋኝና በታዳሚ መካከል የሚደረግ የክዋኔ ተግባቦት የግለሰቡን ማንነት ብቻ ሳይሆን ማኅበረሰቡ የሚጠብቀውን ባህላዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያና ፖለቲካዊ ሰብዕናና እሴት ለመትከል የሚደረግ ጥረት ነው የሚል መደምደሚያ ላይ ተደርሷል። ርዕሰ ጉዳዩ ሰፊ በመሆኑ የባህል ጥናት ዕቅድ ያላቸው አካላት ጥናት ቢያካሂዱበት አዳዲስ ዕውቀቶችን ያበረክታሉ::

Published

2025-07-08

How to Cite

ሙሉ አ. . (2025). የጀግና ብያኔ በለቅሶ ዐውድ ላይ በሚከወን የፉከራ ቃል ግጥም ክዋኔና ይዘት ውስጥ በባህር ዳር ከተማ፣ በሰባታሚት ቀበሌ ማሳያነት. ZENA-LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures), 34(1). Retrieved from https://ejol.aau.edu.et/index.php/JAELC/article/view/12022