የአርጐባ ብሔረሰብ የለቅሶ ሥነ ስርዓት ትንተና፦ ክዋኔው፣ መዋቅሩ፣ ትዕምርቱና ፋይዳው

Authors

  • እታገኘሁ አስረስ[1]፣ ዘሪሁን አስፋው (ተባባሪ ኘሮፌሰር)[2]፣ የኔዓለም አረዶ (ዶ/ር)[3]፣ መሐመድ አሊ (ዶ/ር)[4]

Abstract

 

የጥናቱ ዋና ዓላማ የአርጐባ ብሔረሰብን የለቅሶ ሥነ ስርዓት ክዋኔ፣ መዋቅር፣ ትዕምርትና ፋይዳ መተንተን ነው። የአርጐባ ብሔረሰብ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሐረሪና በአፋር ክልሎች ውስጥ የሚኖር ሲሆን (አህመድ 1999፡ 161) የዚህ ጥናት ትኩረት የአፋሩ አርጐባ ነው። ሥነ ስርዓት "አንድን ድርጊት በተመለከተ የተለመደ ስርኣትን ወይም ደንብን ተከትሎ የሚሄድ ክንውን" (የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዳሚ 2ዐዐ6: 138) ነው። ክዋኔ የተግባቦት ስልት (Bauman 1975: 293)፣ መዋቅር የነገሮች ንዑሳን ክፍሎችና እርስ በርስ ያላቸው ግንኙነት (Storey 128)፣ ትዕምርት ሀሳብን የሚያስተላልፍ ቁስ፣ እንቅስቃሴና ግንኙነት (Geertz qtd.[5] in Turner 1997: 145) ሲሆን ፋይዳ ሥነ ስርዓቱ ለከዋኙ ማኀበረሰብ የሚሰጠው ጠቀሜታ ነው። በጥናቱ የቀደምት ጥናቶች ንባብና የመስክ ስራ ተከናውኗል። በመስክ መረጃ የተሰበሰበባቸው ዘዴዎች ምልከታ፣ ቃለመጠይቅና ቡድን ተኮር ውይይት ሲሆኑ ዓላማ ተኮርና ጠቋሚ የናሙና ዘዴዎች ጥቅም ላይ ውለዋል። መረጃን ለመተንተን ኢትኖግራፊ የጥናት ሞዴል ጥቅም ላይ ውሏል። የጥናቱ ግኝት የብሔረሰቡ የለቅሶ ሥነ ስርዓት ክዋኔ በመለየት፣ ሽግግርና መቀላቀል ሶስት ደረጃዎች ሊከፈል የሚችል መሆኑን፣ ድርጊታዊና (በቀኝ ማስተኛት፣ ጥልፍ መተርተር፣ ሽቶና ውሀ ማርከፍከፍ፣ ቅጠል መጐዝጐዝ፣ የሟችን ሚስት ቅቤ መቀባትና አዲስ ቀሚስ ማልበስ፣ ቆዳን በጠዋት ውሀ አርከፍክፎ ማጠፍ፣ በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ) ቁሳዊ (ውሀ፣ ቆዳ) ትዕምርቶች መኖራቸውን፣ ሥነ ስርዓቱ ተግባቦታዊና ማኀበራዊ (ለቅሶ መድረስ)፣ ኢኰኖሚያዊና (ሀፈሻ) ሥነ ልቡናዊ (በጋራ ማልቀስና ሶደቃ) ፋይዳዎች  ያሉት መሆኑን አሳይቷል። ሀፈሻን ከዘመናዊ የመረዳጃ ተቋማት ጋር ማስተሳሰር ለቀጣይነቱ አስተዋጽኦ ያደርጋል፤ ዚያራ[6]ም በጥልቀት ቢጠና መልካም ነው።  

ቁልፍ ቃላት፣ [አርጐባ፣ ለቅሶ፣ ሥነ ስርዓት፣ ክዋኔ]

 

Downloads

Published

2025-04-10

How to Cite

እታገኘሁ አስረስ[1]፣ ዘሪሁን አስፋው (ተባባሪ ኘሮፌሰር)[2]፣ የኔዓለም አረዶ (ዶ/ር)[3]፣ መሐመድ አሊ (ዶ/ር)[4]. (2025). የአርጐባ ብሔረሰብ የለቅሶ ሥነ ስርዓት ትንተና፦ ክዋኔው፣ መዋቅሩ፣ ትዕምርቱና ፋይዳው . ZENA-LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures), 33(2), 62–91. Retrieved from https://ejol.aau.edu.et/index.php/JAELC/article/view/11607