የሐሳብ ማደራጃ ብልሃቶች (Graphic organizers) አንብቦ የመረዳት ችሎታንና የማንበብ ተነሳሽነትን ለማጎልበት ያላቸው ሚና፤ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

Authors

  • ሰላማዊት ሳፊሳ Bahir Dar University
  • ማረው አለሙ Bahir Dar University
  • ሙሉጌታ ተካ Bahir Dar University

Keywords:

የሐሳብ ማደራጃ ብልሃቶች፣ አንብቦ የመረዳት ችሎታ፣ የማንበብ ተነሳሽነት

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የሐሳብ ማደራጃ ብልሃቶች የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታንና የማንበብ ተነሳሽነትን በማጎልበት ረገድ ያላቸውን ሚና መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ ቅድመትምህርትና ድኅረትምህርት ፈተና ባለቁጥጥር ቡድን ፍትነትመሰል ንድፍን የተከተለ ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በ2013 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር በዶናበርበር የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርትቤት ትምህርታቸውን ከሚማሩ የሰባተኛ ክፍል አምስት ክፍሎች መካከል ከሁለት የመማሪያ ክፍሎች በተራ የዕጣ ንሞና ዘዴ የተመረጡ 114 (58 የፍትነቱና 56 የቁጥጥሩ ቡድን) ተማሪዎች ናቸው፡፡ መረጃዎቹ በአንብቦ መረዳት ፈተናና በማንበብ ተነሳሽነት የጽሑፍ መጠይቅ በቅድመትምህርትና በድኅረትምህርት ከተሰበሰቡ በኋላ በየዓይነታቸው ተደራጅተው በገላጭ ስታቲስቲክስና በልይይት ትንተና (ANOVA) እንዲሁም የቤንፌሮኒ የጉልህነት ማስተካከያ ስሌትን (p = .025) መሰረት በማድረግ በባለብዙ ልይይት ትንተና (MANOVA) ተሰልተው ተተንትነዋል፡፡ ውጤቱም በቅድመትምህርት ተመጣጣኝ አማካይ ውጤቶች ያስመዘገቡት የፍትነቱና የቁጥጥሩ ቡድኖች በድኅረትምህርት የአንብቦ የመረዳት ፈተና (p = .001, partial η2 = .128) በድህረትምህርት የማንበብ ተነሳሽነት የጽሑፍ መጠይቅ (p = .001, partial η2 = .116) የፍትነቱ ቡድን ተሳታፊዎች ከቁጥጥሩ ቡድን ተሳታፊዎች በስታቲስቲክስ ጉልህ የሆነ የመሻሻል ልዩነት አሳይተዋል፡፡ ይህ ውጤትም የሐሳብ ማደራጃ ብልሃቶች የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት በማጎልበት ረገድ ጉልህ ሚና እንዳላቸው አመላክቷል፡፡

Downloads

Published

2024-10-25

Issue

Section

Articles