በክፍል ውስጥ ተራክቧዊ ዲስኩር ውስጥ የዲስኩር አመልካች ‘እሺ’ ሥርጭትና ተግባር ትንተና
Keywords:
ዲስኩር፣ ውሁዳሃድ፣ ዲስኩር አመልካች፣ ግጥምጥምነትAbstract
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በተራክቦአዊ ዲስኩር ውስጥ የእሺን ሥርጭትና ተግባራት መተንተን ነው፡፡ ጥናቱም የተራክቦ ትንተናን ማሕቀፍ መሠረት በማድረግ በክፍል ውስጥ ተራክቧዊ ዲስኩር ላይ የተካሄደ ነው፡፡ የጥናቱ መረጃም ለአንድ የተግባራዊ ሥነልሳንና የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን ማስተማር የሦስተኛ ዲግሪ ማሟያ ጥናት በተቀረጸና ወደጽሑፍ የተቀየረ የክፍል ውስጥ ተራክቦ መረጃ የተወሰደ ነው፡፡ ለትንተና በጥቅም ላይ የዋለውም የምዝግብ መረጃው ሰባ አምስት ገጽ ሲሆን፣ ይህም የመረጃውን ሃያ አምስት በመቶ በላይ (26.22%) ሸፍኗል፡፡ በመረጃውም በአጠቃላይ ከ1171 ተራዎች (turns) በላይ ተጠቃለዋል፡፡ በዚህ መረጃ መሠረት በውሁዳሃዱ ውስጥ አምስት ዲስኩር አመልካቾች 335 ጊዜ ተደጋግመው ገብተዋል፤ ከነዚህ ዲስኩር አመልካቾች ውስጥም ተተኳሪው እሺ 120 (35.82%) ጊዜ ተደጋግሞ ገብቶ ተገኝቷል፡፡ በመረጃው መሠረት እሺ በውሁዳሃዱ ውስጥ ያለው ሥርጭት በአመዛኙ በዓረፍተንግግር/ በዓረፍተነገር መነሻ ላይ 88 ጊዜ (73.33%) ሲሆን፣ ከዚህ በተለየ በዓረፍተንግግር መካከልና መድረሻ ላይ ገብቶ የተገኘው 32 ጊዜ (26.67%) ሆኗል፡፡ በተራክቧዊው ዲስኩር ውስጥ ያሉት ተግባራትም መቀበል፣ መፍቀድ፣ መቀጠል፣ ማጠቃለል፣ መጋበዝ፣ ማተኮር እና ማስቆምና ማስቀጠል የሚሉት ሆነው ተገኝተዋል፡፡ በተለምዶ ማዕቀፍ የሚለውን ቃል ለመተካት የገባ ነው፡፡ ማዕቀፍ በኪዳነወልድ ክፍሌ፣ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሀዲስ መሠረት እንቅፋት ማለት ነው፡፡ ሰለዚህ የእግሊዝኛውን Fraework በአማርኛ በትክክል አይፈታውም፡፡ ሊፈታው የሚችለው ማሕቀፍ (ከማቀፍ፣ ከመያዝ፣ ከመሰብሰብ… የተያያዘ ፍቺ አለው) የሚለው በመሆኑ እዚህ ጥናት ውስጥ በጥቅም ላይ ውሏል፡፡
Downloads
Published
Issue
Section
License
Copyright (c) 2024 Faculty of Humanities-Bahir Dar University
This work is licensed under a Creative Commons Attribution 4.0 International License.