ልዕለአዕምሯዊ የማንበብ ብልሃቶች (Metacognitive Reading Strategies) አንብቦ የመረዳትንና በጥልቀት የማንበብን ችሎታ የማጎልበት አስተዋፅኦ፡- በሰባተኛ ክፍል አማርኛ አፍፈት ተማሪዎች ተተኳሪነት
Keywords:
ልዕለአዕምሯዊ የማንበብ ብልሃቶች፣ አንብቦ የመረዳት ችሎታ፣ በጥልቀት የማንበብ ችሎታAbstract
የጥናቱ ዋና አላማ ልዕለአዕምሯዊ የማንበብ ብልሃቶች አንብቦ የመረዳትንና በጥልቀት የማንበብን ችሎታ የማጎልበት አስዋፅኦ መፈተሽ ነው፡፡ ጥናቱ ፍትነትመሰል ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት ባለቁጥጥር ቡድን የምርምር ስልትን የተከተለ ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በባህርዳር ከተማ በቁልቋል ሜዳ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትቤት በ2011 ዓ.ም በመማር ላይ ከሚገኙ ሦስት የመማሪያ ክፍሎች መካከል በቀላል የዕጣ ንሞና ዘዴ በተመረጡ ሁለት የመማሪያ ክፍሎች የሚማሩ 94 ተማሪዎች ናቸው፡፡ የፍትነቱ ቡድን በልዕለአዕምሯዊ የማንበብ ብልሃቶች፣ የቁጥጥሩ ቡድን ደግሞ በተለመደው የማስተማሪያ መንገድ አንብቦ መረዳትን ለ12 ክፍለጊዜያት ተምረዋል፡፡ መጠናዊ መረጃዎች ከቁጥጥሩ ቡድንና ከፍትነቱ ቡድን ተማሪዎች በቅድመትምህርትና ድኅረትምህርት አንብቦ በመረዳት ፈተናና በጥልቀት በማንበብ ፈተና ተሰብስበዋል፡፡ አንብቦ የመረዳት ችሎታና በጥልቀት የማንበብ ችሎታ መረጃዎች የቤንፌሮኒ የጉልህነት ማስተካከያ ስሌትን (p=.025) መሰረት በማድረግ በባለብዙ ተላውጦ ልይይት (multivariate analysis of variance) ተተንትነዋል፡፡ የድኅረትምህርት መጠናዊ መረጃዎች ውጤቶች እንዳመለከቱት፣ አንብቦ በመረዳት ችሎታ (p = .001, partial η2 = .406)፣ በጥልቀት በማንበብ ችሎታ ደግሞ (p = .001, partial η2 = .515) የፍትነቱ ቡድን ተሳታፊዎች ከቁጥጥሩ ቡድን ተሳታፊዎች በልጠው ጉልህ መሻሻል አሳይተዋል፡፡ በመሆኑም በልዕለአዕምሯዊ የማንበብ ብልሃቶች ማንበብን ማስተማር አንብቦ የመረዳት ችሎታንና በጥልቀት የማንበብ ችሎታን ለማሳደግ አስተዋጽኦ አለው፤ ከሚል መደምደሚያ ላይ ተደርሷል፡፡
Downloads
Published
Issue
Section
License
Copyright (c) 2024 Faculty of Humanities-Bahir Dar University
This work is licensed under a Creative Commons Attribution 4.0 International License.