የተለዋዋጭ ምዘና አቀራረብ በአማርኛ የአንብቦ መረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ላይ ያለው አስተዋፆ በአራተኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

Authors

  • ታረቀኝ ተፈራ Bahir Dar University
  • ማረው አለሙ Bahir Dar University
  • ጥላሁን ግደይ Bahir Dar University

Keywords:

ተለዋዋጭ ምዘና፣ የአንብቦ መረዳት ችሎታ፣ የማንበብ ተነሳሽነት

Abstract

የዚህ ጥናት ዓላማ ተለዋዋጭ ምዘና በአማርኛ አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት ላይ ያለውን አስተዋፆ መመርመር ነበር፡፡ ጥናቱ የተተገበረው በፍትነት-መሰል ምርምር ስልት የቅድመና ድኅረ ትምህርት ፈተና ባለቁጥጥር ቡድን ንድፍ ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በ2013 ዓ.ም. በባሕር ዳር እውቀትፋና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትቤት በሁለት የመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ይማሩ የነበሩ 88 የአራተኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በምርምሩ የተዘጋጀውን ትምህርት ለስድስት ሳምንታት (12 ክፍል ጊዜያት) ተከታትለዋል፡፡ የአንብቦ መረዳት ትምህርቱን፣ የፍትነት ቡድኑ ተማሪዎች በተለዋዋጭ ምዘና አቀራረብ የተማሩ ሲሆን፣ የቁጥጥር ቡድኑ ተማሪዎች ደግሞ በመምህርና በተማሪ መጻሕፍት አቀራረብ መሰረት በተለመደው መንገድ ተከታትለዋል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች ከምርምሩ በፊትና በኋላ ያሏቸው የአንብቦ መረዳት ችሎታና የማንበብ ተነሳሽነት በፈተናና በጽሑፍ መጠይቅ ተለክቷል፡፡ የተገኙት መረጃዎችም በካይ-ካሬ፣ በነጻ ናሙና ልይይት ትንተናና በመዋቅራዊ እኩልዮሽ ሞዴል ተፈትሸዋል፡፡ በትንተና ውጤቱ መሰረትም የማንበብ ትምህርትን በተለዋዋጭ ምዘና ማስተማር በተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ችሎታ (β = .386, p = .018) እና የማንበብ ተነሳሽነት (β = .717, p < .001) ላይ ቀጥተኛ አስተዋፆ አለው፡፡ ስለዚህ ተለዋዋጭ ምዘና በመደበኛ ትምህርት ውስጥ በአማርኛ ቋንቋ አንብቦ መረዳትን ለማስተማር ተግባራዊ ቢደረግ የትምህርት ጥራት ጉድለትን ለማሻሻል አስተዋፆ ይኖረዋል፡፡

Downloads

Published

2024-10-24

Issue

Section

Articles