የባህላዊ አዳኝና የሚታዊ ተጋዳሊ ጉዞ እጣዎች ንጽጽራዊ ትንተና፤ በመለየት ፈለግ መነሻ

A Comparative Analysis of the Traditional Hunter and the Mythic Hero's Departure Journey

Authors

  • Lemma Nigatu Tarekegn Jimma University
  • Mulu Getachew Mengistu Jimma University

Keywords:

መለየት፣ ሚት፣ ባህላዊ አዳኝ፣ ተጋዳሊ፣ ጉዞ, myth, traditional hunter, hero, journey

Abstract

የዚህ ጥናት መሰረታዊ ግብ በሚታዊ ተጋዳሊና በባህላዊ አዳኝ የህይወት እጣ ጉዞዎች የሚታዩ ተመሳስሎዎችንና ልዩነቶችን በማነጻጸር የፎክሎር ጥናት ትንተና ለሁለንተናዊነት (universality) እና አካባቢያዊነት (locality) ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ማሳየት ነው፡፡ ጥናቱ አይነታዊ ሲሆን ኢትኖግራፊያዊ የምርምር ንድፍን ተከትሏል፡፡ ለጥናቱ ከምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ኪረሙና ጉድሩ፤ ከኢሉ አባቦር ዞን፣ ቡሬ፤ ከጅማ ዞን፣ ሰኮሩ ወረዳ በታላሚ ናሙና ተመርጠዋል፡፡ በእነዚህ ወረዳዎች ከሚኖሩ የተጠኚው ማሕበረሰብ አባላት መረጃዎቹ የተሰበበሰቡት በቃለ መጠይቅና በቡድን ተኮር ውይይት ነው፡፡ በቃለ መጠይቅ የተሳተፉት 24 ቁልፍ መረጃ አቀባዮች ሲሆኑ፣በቡድን ውይይት ደግሞ 23 የባህሉ እውቀት ያላቸው ግለሰቦች ናቸው፡፡ ሁሉም የጥናቱ ተሳታፊዎች የተመረጡት በታላሚ እና በጓድ ጥቆማ የንሞና ዘዴዎች ነው፡፡ ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰነዶች ከአብያተ መጻሕፍትና ከሌሎችም ቦታዎች ተሰብስበዋል፡፡ የመረጃዎቹን ምሉዕነትና ትክክለኝነት የማጣራት ስራ ከተከናወነ በኋላ በመለየት ምእራፍ ስር በሚገኙት አምስት ንዑሳን ምዕራፎች ስር ተመድበው ትንተናው ተካሂዷል፡፡ የጥናቱ ውጤትም፣ በገድል ጥሪ፣ ጥሪውን ለመቀበል በሚኖር ፈቃድ (እምብኝታ)፣ በልእለ ተፈጥሮ ረድኤት፣ የመጀመሪያውን እና የመጨረሻውን ቅጽሮች በመዝለቅ፣ በሚታዊ ተጋዳሊና በባህላዊ አዳኝ የእጣ ጉዞዎች መካከል ተመሳስሎ መኖሩን አሳይቷል፡፡ በእነዚህ ምእራፎች ስር ያሉ ዝርዝር ጉዳዮች ሲታዩ ግን፣ በሚታዊ ተጋዳሊና በባህላዊ አዳኝ የዕጣ ጉዞዎች መካከል ባህል ፈጠር ልዩነቶች ታይተዋል፡፡ ይህም የፎክሎር መረጃዎችን ለሁሉም ባህሎች በሚሰራው በሁለንተናዊነት ወይም የየባህሎች ተናጠናላዊ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ በሚያተኩረው አካባቢያዊነት ላይ ብቻ ተመስርቶ መተንተን ጥናቱን የተሟላ እንደማያደርገው ያሳያል፡፡ ስለሆነም የጋራ አካዳሚዊ ዕውቀቶችን ለማዳበርና የየባህሎችን ተናጠላዊ ጉዳዮች ለመረዳት ለሁለቱም ተገቢው ትኩረት ቢሰጥ መልካም ይሆናል፡፡ 

The primary objective of this study is to underscore the necessity of integrating both universality and locality in folklore analysis. By conducting a comparative examination of the mythic hero’s and the traditional hunter’s life journeys, this research highlights their shared motifs as well as culturally distinct variations. Employing a qualitative ethnographic approach, the study focuses on selected communities in Kiramu and Guduru (East Wollega Zone), Bure (Ilu Aba Bor Zone), and Sokoru Woreda (Jimma Zone). Data were systematically collected through in-depth interviews with 24 key informants and focus group discussions involving 23 culturally-knowledgeable participants. Participants were selected using a combination of purposive and snowball sampling techniques to ensure depth and relevance. Supplementary archival materials were also gathered from libraries and other relevant sources. Following a rigorous verification process to ensure data accuracy and completeness, the findings were organized into five analytical subsections. The study reveals striking parallels between the mythic hero’s journey and that of the traditional hunter, particularly in key stages such as: the call to adventure; the acceptance (or refusal) of the call; the intervention of supernatural aid, and the symbolic crossing of thresholds (both initial and final). However, a closer examination of these stages uncovers culturally specific variations, demonstrating that neither a purely Universalist (cross-cultural) nor an exclusively localist (culture-specific) approach suffices for a comprehensive understanding of folklore. Thus, this study advocates for a dual analytical framework—one that balances universal archetypes with local particularities—to advance scholarly discourse and foster a deeper appreciation of both shared narrative structures and unique cultural expressions.

Downloads

Published

2025-07-24