የምርቃን ስርዓተ ከበራ ኃይል በሰሜን ወሎ ማኅበረሰብ
The Power of the Blessing Ritual Practices in the North Wollo Community
Keywords:
ማኅበራዊነት፣ ስርዓተ ከበራ፣ ስነልቦና፣ ኃይል፣ እሴት, Power, Psychology, Ritual practice, Sociality, ValueAbstract
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የምርቃን ስርዓተ ከበራ የሚያስገኘውን ማኅበረ-ስነልቦናዊ ፋይዳ መመርመር ነው፡፡ ስለሆነም የሰሜን ወሎ ማኅበረሰብን ፍልስፍና፣ አስተሳሰብ እንዲሁም አመለካከት ለመረዳት ላቅ ያለ ሚና ይኖረዋል፡፡ ጥናቱ በባህርይው ከአይነታዊ ምርምር የሚዋገን ነው፡፡ በተለያዩ መስፈርቶች ከተመረጡ የመረጃ አቀባዮች በምልከታ ፣ በቃለ መጠይቅ እንዲሁም በቡድን ውይይት የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች የተሰበሰበውን መረጃ በሀቲታዊ ትንተና ስልት እየተተነተነ እና በክዋኔ ንድፈ ሃሳብ እየተመራ ዘልቋል ፡፡ የጥናቱ ግኝት የምርቃን ስርዓተ ከበራ አመክንዮአዊ አስተሳሰብ ላይ የሚመረኮዝ ሲሆን ትኩረቱም ጤንነትን ፣ ተደማጭነትን ፣ አዱኛን ፣ የልጅ ፍሬን እንዲሁም ረጅም እድሜን የሚመኙበት ስርዓታዊ እሳቤ ነው ፡፡ የምርቃን ቱርፋት ተመራቂው ህይወቱን በአርያነት የመምራት፣ ማኅበራዊ ትስስርን የማጠናከር ፣ ቀና የመሆን እንዲሁም ሰዎችን ለመልካም ተግባር የማሰለፍ ኃይልን የሚያጎናጽፍ መሆኑ ተመላክቷል ፡፡ ከዚህም በተሻጋሪ የማኅበረሰብን ማንነት ፣ ስርዓት ፣ አኗኗር ፣ ልማድ ፣ ወግ ፣ ታሪክ ፣ ስነልቦና ፣ ርዕዮተ ዓለም እንዲሁም የህይወት ፍልስፍና ገላጭ ሆኖ የሚቀርብ መሆኑን ጥናቱ ጠቁሟል ፡፡ ምርቃን በተለያዩ ዐውዶች ላይ የሚከወን ቢሆንም በዋናነት ግን ልጅ ሲወለድ ፣ አዲስ ቤት ተሰርቶ ሲገባ ፣ በግጭት አፈታት ስርዓት ፣ በእርሻ ስራ ፣ በሰርግ ፣ ቡና ሲጠጣ እንዲሁም በቱፋታ ስርዓት ላይ የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ምርቃን ከአምላክ እና አላህ ጋር የመገናኛ ድልድይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ እንዲሁም እውነታ ላይ ሲመሰረት በልዕለ ተፈጥሯዊ ኃይል ቅቡል እንደሆነ ይታመናል ፡፡ የምርቃን ስርዓተ ከበራ ማኅበራዊ ፣ ስነ ልቦናዊ ፣ አስተዳደራዊ እንዲሁም አዱኛዊ አበርክቶዎች ያሉት መሆኑን ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ ይሁን እንጂ ምርቃን ለልማት እንዲውል በማድረጉ ሂደት ውስጥ ውስንነት ታይቷል፡፡ በመሆኑም የሀገር ሽማግሌዎች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም የባህል ተመራማሪዎች ምርቃን ለልማት በሚውልበት ሁናቴ ላይ ትኩረት ቢሰጡ መልካም ነው፡፡
The main purpose of this study is to examine the socio-psychological benefits of the blessing ritual practices in the North Wollo community. The study argues that studying blessing rituals plays a significant role in understanding the philosophy, thinking, and attitudes of a given community. To that end, a qualitative research approach and a descriptive research design were employed. The data were collected from selected informants through observation, interviews, and focus group discussions. The study used performance theory. The results of the study indicated that the ritual practice of blessing is based on logical thinking. Moreover, the ritual practice seeks health, honor, prosperity, and longevity. It is indicated that the product of blessing empowers the graduate to lead a noble life, strengthen social relations, be kind, and inspire people to do good deeds. The study also indicated that the blessing ritual is a reflection of the community’’s identity, lifestyle, customs, traditions, history, psychology, ideology, and philosophy of life. Blessing is performed in various contexts; it is mainly mentioned when a child is born, when a new house is built, in conflict resolution systems, during agricultural work, at weddings, when drinking coffee, and during the Tufata system. It is indicated that the blessing is a bridge of communication with God and Allah. It is also believed to be endowed with supernatural powers when based on reality. Moreover, the study indicated that the blessing ritual has social, psychological, administrative, and economic benefits. However, there have been limitations in the process of using the blessing for development. Therefore, it would be good if elders, non-governmental organizations, and cultural researchers paid attention to the way in which the blessing is used for development.