የባህር ኃይል እና የኢትዮጲያ ብሔራዊ ደኀንነት ቅንጦት ወይስ የሕልውና ጉዳይ

Authors

  • ካፒቴን ከበደ ሚካኤል መንገሻ የኢፌዲሪ ባህር ኃይል ምክትል አዛዥ ለትምህርትና ሥልጠና (ተወካይ)
  • አዲስ ዓለማሁ ገብረማሪያም በኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትውት የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ተመራማሪ

Keywords:

ኢትዮጲያ፣ ባህር ኃይል፣ ቀይ ባህር፣ ብሔራዊ ደኀንነት፣ የባህር በር፣ የአፍሪካ ቀንድ

Abstract

በዓለማችን በርካታ ሃገራት የባህር ኃይል የሚያቋቁሙት የባህር ክልላቸውን ለማስጠበቅ ሲሆን ከዚህም ባሻገር ሃገራቱ አለማቀፉን የባህር ደህንነት ለመጠበቅ፤ የባህር ላይ ውንብድናን በመከላከል በምድር አካል ላይ በመሆን ሊመከቱ የማይችሉ የጠላት ኃይል እንቅስቃሴን ለመመከት፤ በዓለም-አቀፉ የባህር ክልል ላይ ለሚደረጉ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና ልማት ላይ ለመሰማራት፤ የባህር ላይ ህገ ወጥ የሰው ዝውውርና የመሳሪያ ሽያጭን ለመቆጣጠር የባህር ሃይላቸውን የሚያጠናክሩበት ሁኔታ አለ። አሁን አሁን የባህር በር የሌላቸው በርካታ የዓለማችን ሃገራት ሳይቀሩ የባህር ኃይል ያቋቋሙበት ሁኔታ መኖሩን መረዳት ይቻላል። በዓለማችን ላይ የባህር በር ያላቸውም የሌላቸው ሃገራት በተመሳሳይ የንግድ መርከቦቻቸውን ደህንነት መጠበቅ፤ ለሁሉም ክፍት የሆነውን ዓለም-አቀፍ የባህር እና የውቅያኖስ አካልን መጠቀም፤ ሽብርተኝነትና እና የባህር ላይ ውንብድናን መከላከል ይጠበቅባቸዋል። ኢትዮጲያ ከታላላቅ የአለማችን የውሃ አካል (ቀይ ባህር እና ህንድ ውቅያኖስ) ያልራቀችና በቅርብ ርቀት የምትገኝ ሃገር ነች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአለማችን ሃያላን ሃገራትን ጨምሮ በርካታ የባህረ ሰላጤው ሃገራት በአፍሪካ ቀንድ (በቀይ ባህርና በህንድ ውቅያኖስ ዳርቻዎች) የወደብ ግንባታ እና የወታደራዊ ጦር ሰፈር ምስረታ
ፉክክር ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል። ሃገራችን ኢትዮጲያ በቀጠናው ያለው የሃገራቱ የጦር ሰፈር ምስረታና የወደብ ግንባታ እሽቅድድም ነገሮችን በጥሞና በመመልከት ለንግድ መርከቦቿ ደህንነት እና በአካባቢው ያለው ፉክክር ወደ ፊት ሊያመጣ የሚችለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ግምት ውስጥ በማስገባት የኢትዮጲያን ብሄራዊ ጥቅም እና የንግድ መርከቦቿን ደህንነት አስተማማኝ በሆነ መንገድ ለማስጠበቅ በአዋጅ ቁጥር 1100/2011 መሰረት የኢትዮጲያ ባህር ኃይል የመከላከያ ሃይሎች አካል ሆኖ ተቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል። ይህ ጥናትም በዋነኛነት በኢትዮጲያ የባህር ኃይል መቋቋሙ እንድምታውን የሚዳስስ ሲሆን በኢትዮጲያ የባህር ኃይል መቋቋም ላይ ያሉ አዎንታዊ እና አሉታዊ አመለካከቶች ላይ ጥልቅ ዳሰሳ በማድረግ ባህር ኃይል ለኢትዮጲያ ቅንጦት ወይስ የህልውና ጉዳይ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ነው። የጥናቱ መነሻ ችግርም በኢትዮጲያ የባህር ኃይል እንዲቋቋም መደረጉ የተለያዩ አካላት፣ ሚዲያዎች እና ዜጎች የተለያየ አዎንታዊ፣ አሉታዊ እና የተዛቡ ምልከታቸውን እያንጸባረቁ ይገኛሉ። ይህን እንደ ጥናት የባህር ኃይልን አስፈላጊነት የሚዳስስ፣ በቀጠናው ያሉ የሃያላን ሽኩቻና በባህር ኃይል መመስረት ዙሪያ የሚታዩ የተዛቡ አመለካከቶች እንዴት መቅረፍ እንደሚቻልም በጥልቀት በማጥናት የኢትዮጲያን የውሃ ላይ
ደህንነት እና ብሄራዊ ጥቅም ማስጠበቅ የሚችል ተወዳዳሪ የሆነ ባህር ኃይል ለመገንባት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ምክረ-ሃሳቦችን ለማቅረብ ያለመ ነው።

Published

2024-11-16