ጥቅምት 15 ለምን የሠራዊት ቀን ሆኖ ይከበራል?

Authors

  • ኮሎኔል መስፍን ለገሠ ደበሌ በኢፌዲሪ መከላከያ የጥናትና ምርምር ማዕከል ባልደረባ የነበሩ

Keywords:

የሠራዊት ቀን፣ የኢትዮጲያ መከላከያ ሠራዊት፣ ጥቅምት 15፣ ታሪክ

Abstract

ኢትዮጲያ የባለ ብዙ ታሪክ አገር ብትሆንም በታሪክ ድርሳናት አብዛኛውን ቦታ ይዞ የምናገኘው ግን የጦርነት ታሪክ ነው። ከነዚህ የጦርነት ታሪኮቻችን ውስጥ ኢትዮጲያን በተለያዩ ጊዜያት ሊወሩ ከመጡ ባዕዳን ወራሪዎች ጋር የተደረጉ ጦርነቶች በርካታ ናቸው። በነዚህ ሁሉ ጦርነቶች የኢትዮጲያ ሠራዊት ተጋድሎ አድርጎ፣ የአካልም የሕይወትም መስዋዕትነት ከፍሎ ዛሬ ያለችውን ኢትዮጲያን አስረክቦን አልፏል። አሁንም በዚህ ዘመን ኢትዮጲያን እንደ አገር ለማቆየትና የሕዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ ሠራዊቱ አገሩና ወገኑ ከሱ የሚጠብቁትን በምንም የማይተመን መስዋዕትነት ያለስስት አየከፈለ ይገኛል። ሠራዊት እንዲህ አይነት መስዋዕትነት እንዲከፍል የጥንካሬው ምንጭ ሕዝብ ነውና፣ መስዋዕትነት የሚከፈልለት ሕዝብም ሠራዊቱን በተለያዩ ጉዳዮች በመደገፍ፣ ሞራልና ስነልቦናው ተጠብቆ እንዲቆይ በማበረታታት፣ ለሠራዊቱ ያለውን እለኝታነትና ጥልቅ ፍቅር ይገልፃል፣ ለሚከፍለው መስዋዕትነትም እውቅና ይሰጣል። ሠራዊት ለሚከፍለው መስዋዕትነት ዘወትር ክብር መስጠት ተገቢ ቢሆንም የተለያዩ መነሻዎችን መሰረት አድርጎ ከዓመቱ ቀናት አንዱን የሠራዊት ቀን አድርጎ በብሔራዊ ደረጃ ማክበር በዓለማችን በበርካታ አገራት የተለመደ አሰራር ነው። የኢፌዴሪ መከለካያ ሚኒስቴርም ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጲያ መከላከያ ሠራዊት ቀን በየዓመቱ ጥቅምት 15 ቀን እንዲከበር ወስኗል። በመሆኑም ይህ አጭር ጵሁፍ የሠራዊት ቀንን አስፈላጊነትና በተለይ የሠራዊት ቀን አመራረጥን በተመለከተ የተወሰኑ የውጭ አገራት ተሞክሮዎችን በአጭሩ በመዳሰስ፣ ከአገራችን ታሪክ ውስጥ ደግሞ ለሠራዊት ቀን ሊሆኑ የሚችሉ ታሪካዊ ኩነቶችን ቃኝቶ ጥቅምት 15 የሠራዊት ቀን ሆኖ እንዲከበር የተወሰነበትን መነሻ የሚያቀርብ ይሆናል።

Published

2024-11-16