በሂደተዘውግ አቀራረብ መጻፍን መማር የተማሪዎችን አስረጂ ድርሰት የመጻፍ ችሎታ፣ በትብብር የመጻፍ አመለካከትና የመጻፍ ግለብቃት እምነት ለማጎልበት ያለው አስተዋፆ፤ በአማርኛ ትምህርት በዘጠነኛ ክፍል ተተኳሪነት

Authors

Keywords:

ሂደተዘውግ አቀራረብ፣ በትብብር የመጻፍ አመለካከት የመጻፍ ግለብቃት እምነት

Abstract

This study investigated the impact of a process-genre approach on ninth-grade students' expository essay writing skills, collaborative writing attitudes, and self-efficacy beliefs at Tana Haik General Secondary School in Bahir Dar City. A quasi-experimental design with a pre-test, post-test, and comparison group was employed. The experimental group (n=53) received instruction in a process-genre approach over 12 weeks, while the comparison group (n=53) followed the grade-level curriculum. Data were collected through expository essay tests and questionnaires assessing attitudes toward collaborative writing and self-efficacy beliefs. Results of a between-subjects ANOVA revealed significant improvements in the experimental group compared to the comparison group in expository essay writing ability (p < .001, partial η² = .272), collaborative writing attitudes (p < .001, partial η² = .727), and self-efficacy beliefs (p < .001, partial η² = .698). These findings suggest that a process-genre approach can effectively enhance students' expository writing skills, foster positive collaborative attitudes, and boost self-efficacy in Amharic language.

የዚህ ጥናት ዓላማ በሂደተዘውግ አቀራረብ መጻፍን መማር የተማሪዎችን አስረጂ ድርሰት የመጻፍ ችሎታ፣ በትብብር የመጻፍ አመለካከትና የመጻፍ ግለብቃት እምነት ለማጎልበት ያለውን አስተዋፆ መፈተሽ ነበር፡፡ ለዚህም ቅድመ-ድኅረትምህርት ፈተና ባለማወዳደሪያ ቡድን ፍትነትመሰል ስልት ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በባሕር ዳር ከተማ ጣና ሐይቅ አጠቃላይ ኹለተኛ ደረጃ ትምህርትቤት በ2016 ዓ.ም. በመማር ላይ ከሚገኙ 20 የዘጠነኛ ክፍል መማሪያ ክፍሎች መካከል በቀላል እጣ ንሞና በተመረጡ ኹለት የመማሪያ ክፍሎች የሚማሩ 106 ተማሪዎች ነበሩ፡፡ የፍትነቱ ቡድን ተሳታፊዎች (53 ተማሪዎች) በሂደተዘውግ የመጻፍ ትምህርት አቀራረብ፣ የማወዳደሪ ቡድኑ ተሳታፊዎች (53 ተማሪዎች) ደግሞ በመደበኛው ሥርዓተትምህርት በቀረቡ የመጻፍ ትምህርት ተግባራት መሠረት ለ12 ክፍለጊዜያት (በ12 ሳምንታት) የመጻፍ ትምህርት ተምረዋል፡፡ የቅድመ-ድኅረትምህርት መረጃዎች በአስረጂ ድርሰት የመጻፍ ችሎታ ፈተና፣ በትብብር የመጻፍ አመለካከትና በመጻፍ ግለብቃት እምነት የጽሑፍ መጠይቆች ተሰብስበዋል፡፡ መረጃዎቹ በነፃ ናሙና ልይይት ትንተና (between subjects ANOVA) ተተንትነዋል፡፡ የጥናቱ ውጤት እንዳመላከተው የፍትነቱ ቡድን ተሳታፊዎች በአስረጂ ድርሰት የመጻፍ ችሎታ (P < .001, partial  =.272)፣ በትብብር በመጻፍ አመለካከት (P < .001, partial  = .727) እና በመጻፍ ግለብቃት እምነት (P < .001, partial  = .698) ከማወዳደሪያ ቡድን ተሳታፊዎች በልጠው ጉልህ መሻሻል አሳይተዋል፡፡ ከዚህም በሂደተዘውግ አቀራረብ በአማርኛ መጻፍን መማር የተማሪዎችን አስረጂ ድርሰት የመጻፍ ችሎታ፣ በትብብር የመጻፍ አመለካከትና የመጻፍ ግለብቃት እምነት ለማሳደግ ጉልህ አዎንታዊ አስተዋፆ እንዳለው ለመረዳት ተችሏል፡፡

Downloads

Published

2024-12-18

Issue

Section

Articles