የመካከለኛው ዘመን ኢትዮጵያ የግእዝ ድርሳናት ፍልስፍናዊ ፋይዳ

Authors

  • ዳዊት ግርማ Debre Birhan University
  • ሳሙኤል ጌትነት Addis Ababa University

Keywords:

የኢትዮጵያ ፍልስፍና፣ የግእዝ ፍልስፍናዊ መጻሕፍት

Abstract

የዚህ ጥናት ዓላማ ዘመን ተሻጋሪ የግእዝ ድርሳናት ላይ ፍልስፍናን ማጥናት፤ የፍልስፍና ድርሳናቱን ፋይዳ መመርመር ነው፡፡ ከፍልስፍና ጽሑፎች ውስጥ ፊሳልጎስ፣ ስክንድስ፣ አንጋረ ፈላስፋ፣ ሐተታ ዘርዓ ያዕቆብና ሐተታ ወልደ ሕይወት በጥናቱ ተካተዋል፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሶስቱ የፍልስፍና መጻሕፍት በዘይቤና ተምሳሌት ከፊል ኢትዮጵያዊ ሆነው ተወርሰዋል፡፡ ፍልስፍናዊ ይዘት ያላቸው እሳቤዎች ድርሳናቱ ውስጥ ተዳስሰዋል፡፡ ዲበ አካላዊነት፣ ሥነ ዕውቀት፣ ሥነ አመክንዮ፣ ሥነ ምግባር የመሰሉ የፍልስፍና የጥናት ዘርፎችን እንደንድፈ ሐሳባዊ መቀንበቢያ በመጠቀም በገላጭ ሥነ-ዘዴ የሰነድ ትንተናን እንደ ስልተ ጥናት ይተገብራል፡፡ ድርሳናቱ በጥልቅ ፍልስፍናዊ ይዘት ከመርቀቃቸውም በላይ ለኢትዮጵያ ፍልስፍና ፋይዳቸው ጉልህ ነው፡፡ ዘርዓ ያዕቆብ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ፈላስፋ ሆኖ ዘመናዊ ፍልስፍናን እንደነ ዴካርት ካሉ ታዋቂ የምዕራቡ ዓለም ፈላስፋዎች ተነጻጻሪ ሆኖ በኢትዮጵያ ጀምሯል፡፡ ደቀ መዝሙሩ ወልደ ሕይወትም የመምህሩን አስተምህሮ ቀጥሎ የራሱን አሰላስሎት አክሎ አስፋፍቶታል፡፡ ከተጠቀሱት የፍልስፍና መስኮች በተጨማሪ እንስታዊነትና የሃይማኖት ፍልስፍና የሚንጻባረቅበት እሳቤዎችን ሁለቱ ዘመናዊ ኢትዮጵያውያን ፈላስፎች መርምረዋል፡፡ ጥናቱ በጥንታዊ የግእዝ የሥነ ጽሑፍ ስራዎች ውስጥ ፍልስፍና መኖሩን፤ የታወቁት የፍልስፍና ድርሰቶችና ፍልሱፋኑም ከዘመናዊ ፍልስፍና አንጻር ተፈትነው ምሉዕመሆናቸውን አጽንቶ ለሀገራችን የፍልስፍና፣ የጥበብና በነጻነት የማሰላሰል ታሪክም ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እንዳላቸው ድምዳሜ ላይ ይደርሳል፡፡

Downloads

Published

2024-10-24

Issue

Section

Articles