የሰው ልጅ ኑባሬ ቅኝት በገ/ክርስቶስ ደስታ መንገድ ስጡኝ ሰፊ የግጥም መድብል

Authors

  • በላይነህ ታዬ ገድፈው University of Szeged

Keywords:

ህላዌ፣ ስፍራ፣ ኑባሬ፣ ገ/ክርስቶስ ደስታ፣ ጊዜ

Abstract

ይህ ጥናት በገ/ክረስስቶስ ደስታ (1998) “መንገድ ስጡኝ ሰፊ”  በተሰኘው የግጥም ስራ የሰው ልጅ ኑባሬ (Being) በምን መልክ ተገለፀ በሚለው ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርጓል፡፡ በዚህ ቅኝት በገ/ክርስቶስ የተለያዩ ግጥሞች መካከል ትስስር በመፍጠር  ለሰው ልጅ ኑባሬ መገለጫ ሆነው የቀረቡ መሰረታዊ ህግጋቶችን (categories) መርምሮ ያወጣል፤ በህግጋቶች ኑባሬ ስለተገለጠበት ሁኔታ ትርጉም ይሰጣል፡: ለዚህም ሲባል አንድምታ (hermeneutics) የደራሲው ሀሳብ ምልዓት (content) ሳይዛባ በግጥሞች ውስጥ ባሉ ቃላት፣ በስንኞች እንዲሁም በተለያዩ ግጥሞች መካከል ትስስር በመፍጠር ትርጉም ለመስጠት በማስቻሉ የጥናቱ ስነ-ዘዴ ሆኖ አገልግሏል፡፡ በዚህ ስነ-ዘዴ ከገ/ክርስቶስ 60 አካባቢ ከሚሆኑ ግጥሞች ውስጥ ከጭብጣቸው አንፃር ለጥናቱ ያስፈለጉት ትርጉምና ትንተና ተሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህ መሰረት፣ ለገ/ክርስቶስ ኑባሬ በመሰረታዊነት ግላዊ ሲሆን በቅይይረዊ ጊዜ (temporal time) እና ህላዌ-ስፍራ (existentialle space) መሳክነት (continuum) የሚገነባ የመኖራችን ማሳያ መሆኑን ጥናቱ በግጥሞቹ የጭብጥ ትረጉም አሳይቷል፡፡ 

Downloads

Published

2024-10-24

Issue

Section

Articles