የማኅበራዊ ደረጃ መልክ በወሎ አዝማሪዎች

Authors

  • አስቴር ሙሉ Bahir Dar University

Keywords:

ወሎ፣ አዝማሪ፣ ማህበራዊ ደረጃ

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የወሎ አዝማሪዎችን ማህበራዊ ደረጃ መፈተሽ ነበር፡፡ ይህ ዓላማ ግቡን እንዲመታ በስሩ አዝማሪዎች ለራሳቸው ያላቸው አመለካከት ምንድን ነው? በአዝማሪዎች መካከል ያለው ማህበራዊ ደረጃ ምን ይመስላል? አዝማሪዎች ለሌላው ሰው ያላቸው አመለካከት ምን ይመስላል?  ሌላው ሰው ለአዝማሪዎች ያለው አመለካከት ምንድን ነው? አዝማሪዎች ከሌላው ማህበረሰብ ጋር ያላቸው ማህበራዊ ግንኙነት ምን መልክ አለው?  የሚሉ ጥያቄዎች ተዘጋጅተው ምላሽ አግኝተዋል፡፡ ጥያቄዎችን ለመመለስ የረዱ መረጃዎች ከቀዳማይና ከካልኣይ የመረጃ ምንጮች በምልከታ፣ በቃለመጠይቅና፣በተተኳሪ ቡድን ውይይትና በንባብ  ተሰብስበዋል፡፡ የተሰበሰቡ መረጃዎች በአግባቡ ከተመረመሩ በኋላ የዓላማ ጥያቄዎችን በሚመልስ መልክ በይዘታቸው ተመድበው በክዋኔያዊና ማርክሳዊ ዘዴዎች ተተንትነዋል፡፡ ከትንታኔው  የወሎ አዝማሪዎች የራሳቸውን መንደር መስርተው እንደኖሩ፣ ከጋብቻ አንፃር ሲታዩ ቀደም ባለው ጊዜ እርስ በእርስ ብቻ ይጋቡ እንደነበሩ፣ በመካከል ያለው የፆታ ግንኙነት በመከባበርና በመተባበር ላይ የተመሰረተ እንደሆነ፣ አዝማሪዎች ስለራሳቸው በሙያቸው የተነሳ የተመረጡና የተሻሉ ሆነው እንደተፈጠሩና እንደሚኖሩ አድርገው እንደሚያምኑ፣ በአዝማሪዎች መካከል ጎበዝ አዝማሪና ጎበዝ ያልሆነ አዝማሪ እንዲሁም ባላባትና ጭሰኛ የሚባሉ ደረጃዎች መኖራቸውን አዝማሪዎች በዙሪያቸው ያለው ሌላው ማህበረሰብ ከእኛ በዕውቀት ያነሰ ነው የሚል አመለካከት እንዳላቸው፣ ዛሬ ከሌላው ማህበረሰብ ጋር ያላቸው ማህበራዊ ግንኙነት ከጥንቱ የተሻለ ቢሆንም እኩል አለመሆኑን  ለማየት ተችሏል፡፡

Downloads

Published

2024-10-24

Issue

Section

Articles