የድህረ ቅኝ ግዛት ጭብጦች ትንተና በመንግሰቱ ለማ ፀረ ኰሎኒያሊስት ተውኔት
Keywords:
የድህረ ቅኝ ግዛት ሂስ፣የአውሮፓ ማዕከላዊነት፣የምዕራብ-ምሥራቅ ፍረጃ፣የገዥ-ተገዥ ድልድልAbstract
ይህ ጥናት “የድህረ ቅኝ ግዛት ጭብጦች ትንተና በመንግስቱ ለማ ፀረ ኮሎኒያሊስት ተውኔት” በሚል ርዕስ የተከናወነ ነው። በጥናቱ ከተጠኝ ተውኔቱ የተቀነጨቡ ሃሳቦችን በማቅረብ የንድፈ ሃሳባዊ ዳራውን ገቢራዊነት ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ በጥናቱ ተውኔቱን በምን መሥፈርት እንደተመረጡ፣ በምን ዘዴ እንደተነተኑ፣ የመረጃ ምንጮችንና የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎችን እንዲሁም የመረጃ አተናተን ስልትና ሂደት ቀርቧል። ጥናቱን ለመተንተን የድህረ ቅኝ ግዛት ሥነ ጽሑፍ ንድፈ ሃሳብ ጥቅም ላይ ውሏል። በጥናቴም በተውኔቱ ውስጥ የድህረ ቅኝ ግዛት ሥነ ጽሑፍ መገለጫ ጭብጦች በምን መልኩ እንደተከሰቱ አሳይቷል። ይህ ጥናት ከተውኔቱ ውስጥ ተቀንጭበው በሚቀርቡ ማሳያዎች ላይ በመመስረት ከአውሮፓ ማዕካላዊነት (eurocentirism)፣ከምዕራብ-ምሥራቅ ፍረጃ (orientalism)፣ ከባይተዋርነት (unhomeliness)፣ ከራስን አለመሆን (Mimicry)፣ ከገዥ-ተገዥ ድልድል (Hegemony) እና ቋንቋ፦ድምፅ አልባው ጠመንጃ ከሚሉት ጭብጦች አንፃር ትንታኔ በመስጠት የድህረ ቅኝ ግዛት የሥነ ጽሑፍ ንድፈ ሃሳብ መገለጫዎችን አሳይቷል። በአጠቃላይ ፀረ ኰሎኒያሊስት የተሰኘው ተውኔት የድህረ ቅኝ ግዛት የሥነ ጽሑፍ ንድፈ ሃሳብ መገለጫዎችን የሚያሟላ መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል።
Downloads
Published
Issue
Section
License
Copyright (c) 2024 Faculty of Humanities-Bahir Dar University
This work is licensed under a Creative Commons Attribution 4.0 International License.