የጥቁር አንበሳ ጦር ወታደራዊ አስተምህሮት እና ውርሱ
DOI:
https://doi.org/10.63990/edjss.v3i1.14008Abstract
በታደሰ ሜጫ የተሰናዳው “ጥቁር አንበሳ በምዕራብ ኢትዮጵያ” መጽሐፍ፣ በኢትዮጵያ ዘመናዊ
ወታደራዊ ታሪክ ውስጥ እምብዛም ትኩረት ያልተሰጠውን ነገር ግን ስትራቴጂያዊ ፋይዳው የላቀውን
የ“ጥቁር አንበሳ” ንቅናቄን የሚዘግብ ቀዳሚ የታሪክ ድርሳን ነው። መጽሐፉ ከታሪካዊ ትረካ ባለፈ፣
በ1928 ዓ.ም. የኢትዮጵያ መደበኛ ጦር ከፈረሰ በኋላ የተፈጠረውን ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ክፍተት
ለመሙላት የተሞከረበትን የጀግንነት ጥረት ያሳያል። የደራሲው ዓላማ በወቅቱ በነበረው ወታደራዊ
እንቅስቃሴ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የተሳተፉ አርበኞችን ገጽታ እና ገድል ለትውልድ ማቆየት
ቢሆንም (xviii)፣ ሰነዱ ግን ለወታደራዊ ሳይንስ ተመራማሪዎች ከዚያ የላቀ የወታደራዊ አስተምህሮት
መሠረት ይዟል።
Published
2026-10-31
Issue
Section
Book Review