በመረጃና ድኅነት ተቋማት ውስጥ የምርምር እና ልማት፦ አወቃቀሮች፣ ሂደቶች እና ብሔራዊ አቀራረቦች ንፅፅራዊ ትንተና

Authors

  • ጉደታ ከበደ አስፋዉ የብሔራዊ ደኅነት ዩኒቨርስቲ ሌክቸረር

DOI:

https://doi.org/10.63990/edjss.v3i1.14007

Keywords:

የመረጃና ድኅነት ተቋማት፣ የምርምር እና ልማት አወቃቀሮች፣ የምርምር እና ልማት ሂደቶች፣ የምርምር እና ልማት ብሔራዊ አቀራረቦች

Abstract

የዚህ ጽሑፉ ዓላማ በተለያዩ የመረጃና ድኅነት ተቋማት ውስጥ ምርምር እና ልማት እንዴት
እንደተዋቀረ፣ እንደሚተዳደር እና የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገለት እንደሚተገበር ያለበትን ሁኔታ
የሚመረምር ሲሆን፤ በተለይም ዩናይትድ ስቴትስ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ እስራኤል፣ ፈረንሳይ፣ ቱርክ፣
ቻይና እና ደቡብ አፍሪካን እንደ ዉሰን ጥናቶች (case studies) ማሳያ አድርጎ በመዉሰድ ነዉ። ይህ
ጥናት የመረጃና ድኅነት ተቋማትን፣ ምርምር እና ልማትን በዋነኝነት፤ በሚስጥር እና በሕግ ገደቦች
ሁኔታዎች ውስጥ ባሉ ደረጃዎች፣ ለብሔራዊ ደህንነት ቅድሚያ በሚሰጣቸውን ነገሮችን ወደ ሳይንሳዊ፣
ቴክኖሎጂያዊ እና ትንታኔያዊ ችሎታዎች የሚቀይር በተልዕኮ ላይ የተመሰረተ የዑደት ሂደት አድርጎ
ይገልጸዋል። ጽሑፉ የተለመዱ የድርጅታዊ ሞዴሎችን በተለይም የተማዕከለ የሳይንስ እና የቴክኖሎጂ
ዳይሬክቶሬቶች (centralized Science and technology directorates) ፣ የተካተቱ
የቴክኒክ ቡድኖች፣ በተቋማት መካካል የሚደረግ የምርምርና ልማት (Interagency Research
and Development) አደረጃጀት እና አጋርነት ላይ ያተኮሩ የፈጠራ ሥነ-ምህዳሮችን፤ እንዲሁም እንደ
ሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት፣ የሳይበር ኦፕሬሽንስ፣ ክሪፕቶግራፊ፣ የኳንተም ቴክኖሎጂዎች እና ትላልቅ
የመረጃ ትንተናዎች ያሉ አገራዊ አቀራረቦችን የሚቀርፁ አዳዲስ ዘርፎችን ይተነትናል። በተጨማሪም
በምስጢር እና በትብብር መካከል ያለውን ውጥረት፣ የግዥ ግትርነት (procurement rigidity) ፣
ለቴክኒካል ተሰጥኦ ውድድር እና ከላቁ የመረጃና ድኅነት ቴክኖሎጂዎች ጋር የተያያዙ የሥነምግባር እና
የግላዊነት ስጋቶችን ጨምሮ፣ ያሉትን ተሻጋሪ ተግዳሮቶችን ይዳስሳል። የንጽጽር ትንተና (comparative
case) መንገድን በመጠቀም፣ ይህ ጽሑፉ ማዕከላዊ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫን ከተከፋፈለ ፈጠራ እና
ከተዋቀሩ ውጫዊ ሽርክናዎች ጋር የሚያመጣጥን ወደ ድብልቅ የምርምር እና ልማት ስርዓቶች
እየተደረገ ያለ ዓለም አቀፍ ሽግግርን የሚያሳይ ሲሆን፤ የፖለቲካ ስርዓቶች እና የሃገራት ስትራቴጂካዊ
ባህሎች በክትትል፣ በተጠያቂነት እና በረጅም ጊዜ በቴክኖሎጂ ራስን በራስ የማስተዳደር ሂደት ላይ
እንዴት ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉበትን ሁኔታ አጉልቶ ያወጣል።

Published

2026-10-31