ZENA-LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures)
https://ejol.aau.edu.et/index.php/JAELC

The Zena-Lissan Journal was started in 1996 by the then Ethiopian Languages Research Centre (ELRC), now the Academy of Ethiopian Languages and Cultures (hereafter AELC), focused especially on the cultures (folklores) and languages of different societies within Ethiopia. Since then, the journal has continued to be published biannually in Amharic and English languages aimed to encourage research and promote dialogue among scholars of interdisciplinary fields.

Center for Ethiopian Languages and Cultures
en-US
ZENA-LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures)
2222-6028

ስፌት ተኮር ትምእርታዊ ጉዳዮች ትንተና በደቡብ ወሎ ዞን የተመረጡ ወረዳዎች
https://ejol.aau.edu.et/index.php/JAELC/article/view/11597

አጠቃሎ

የጥናቱ ዓቢይ ዓላማ በተመረጡ የደቡብ ወሎ ወረዳዎች ያለውን የስፌት ትምእርታዊ ጉዳዮችን መመርመር ነው፡፡ መረጃዎች ከቀዳማይ እና ከካልዓይ ምንጮች በተለያዩ ዘዴዎች ተሰብስበው ተሰብስበዋል፡፡ ዓይነታዊ የምርምር ስልትን በመከተል የሥነ ትዕምርት ንድፈ ሃሳቦችን መሰረት በማድረግ፤ የፍሮይድ የአዕምሮ መዋቅራዊ ሞዴል የሆኑትን የስብዕና መዋቅሮች ማብራሪያ ሞዴሎች አኳያ በመፈተሽ፤ በይዘት ትንተና እና በትርጓሜ ስልት ተተንትነው ቀርበዋል፡፡ በትንታኔው መሰረት የጥናቱ ማኅበረሰብ ዘንድ የሚስተዋሉት የስፌት ተግባራት ትዕምርታቸው በፍካሬና በእማሬ የሚገለጽ ሲሆን፣ ሙያ፣ ሙያተኛ፣ ግብዓቶች፣ መሥሪያዎች እና ምርቶች ጋር መመሰያዎቹ የተያያዙ ናቸው፡፡ የመመሰያዎቹ አወካከልም ምስስሎሻዊ (resemblance)፣ ስምምነታዊ (symbolic) እና ምክንያታዊ (index) እንደሆነ ጥናቱ ያሳያል፡፡ ከስፌት ጋር ግንኙነት ያላቸው የፍካሬ ልቦና ጉዳዮች ሁለት መልክ ያላቸው ሲሆን፣ እነሱም የፍሮይድ የሰብዕና መዋቅሮች እና መንስኤዎች ናቸው፡፡ በኢድ የሰብዕና መዋቅር ሥነሕይወታዊ ጉዳዮች ሲጠቀሱ፣ በኢጎ ደግሞ ሥነልቦናዊ ጉዳዮች ይጠቀሳሉ፡፡ እንዲሁም በልዕለ ኢጎ ማኅበረ-ባህላዊ እና ግብረገባዊ ጉዳዮች ይጠቀሳሉ፡፡ ከስፌት ጋር በተያያዘ የተስተዋሉት ሥነቃላዊ ጉዳዮች ስር የክልከላ ንግግሮች፣ ፈሊጦች፣ ቃል ግጥሞች እና ተረኮች ሲጠቀሱ፣ ይዘታቸውም ከሙያዎቹ፣ ከሙያተኛው፣ ከግብዓት፣ ከመሥሪያ መሣሪያ፣ ከምርቶቹ ምንነት፣ ከተግባርና አጠቃቀም አውድ ጋር የተያያዙ ትዕምርታዊ ጉዳዮችን ማንጸባረቂያ መሆናቸውን ጥናቱ አመልክቷል፡፡ በጥናቱ የተስተዋሉ አዎንታዊ ግኝቶችን ሊያስቀጥሉ የሚችሉ፣ ከስፌት ጋር የተያያዙ ለውጦች፣ ቀጣይነቶች እና ጾታ ተኮር ጉዳዮችን በስፋትና በጥልቀት ጥናት ቢደረግ የሚሉ ምክረሃሳቦች በአጥኚው ተሰንዝረዋል፡፡

ቁልፍ ቃላት፤ [ስፌት፣ ትዕምርት፣ አወካከል፣ ሰብዕና]

ብርሃኑ ቦጋለ ተስፋዬ
Copyright (c) 2025
2025-04-10
2025-04-10
33 2
1
29

‘ሥነጥበብ ለሥነጥበብነቱ’ ወይንስ ለኅብረተሰባዊ ግልጋሎት? ከአፍላጦን እስከ አልቤር ካሙ
https://ejol.aau.edu.et/index.php/JAELC/article/view/11606

የዚህ ጽሑፍ ቀዳሚ ዓላማ “ሥነጥበብ ለሥነጥበብነቱ ወይንስ ለኅብረተሰባዊ ግልጋሎት?” በሚል ርእስ ሲካኼድ የኖረውን ሙግት መዳሰስ ሲኾን፣ በተጨማሪም በጥያቄው ላይ ያለንን አተያይ ለማጋራት እንሞክራለን። ምርምራችንን ስናስኬድ ወደ ተለያዩ ዘርዘር-ያሉ የአስተሳሰብ ጎዳናዎች የምንገባ ቢኾንም፣ ዋነኛውን ጥያቄኣችንን አንዘነጋም፤ የጥናታችንን አካኼድም ሰፋ ካለ የሐሳብ አድማስ እና ከፍ ካለ የአመለካከት ድባብ “አስገብተን” ለማየት እንሞክራለን። በዚህ ጥናት ዋነኛውን ርእሰጉዳይ የምንዳስሰው ከጥንታውያኑ የግሪክ ፈላስፎች (አፍላጦን እና አሪስጣጣሊስ) ተነሥተን፣ ከዚያ በዐሥራዘጠነኛው መቶ ክፍለ-ዘመን በሩሲያ የተከሠተውን ሙግት (ፕሌኻኖፍ፣ ቸርነቸቭስኪ፣ እና ብሊንስኪ) አይተን፣ በመቀጠል በኻያኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ኹለት ዕውቅ የሥነጽሑፍ እና የፍልስፍና ሰዎች (ሲ. ኤስ. ሉዊስ እና አልቤር ካሙ) ያቀረቡትን ሐሳብ በመቃኘት ነው። የሥነጥበብ ፋይዳን በተመለከተ በዐሥራዘጠነኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ሩሲያ እና በከፊል ፈረንሳይ ሀገር በእጅጉ የጋለ ክርክር የተነሣበት ቢኾንም፣ የጥያቄው አሻራ በጥንታዊት ግሪክ ዘመን እንደነበር እናሳያለን። ከዚህ አኳያ፣ አፍላጦን ሥነጥበብ ላይ ያለውን ጠበቅ ያለ ሒስ አንስተን፣ በአንጻሩ የአሪስጣጣሊስን ሐተታ እና ምላሽ እናቀርባለን። በኹለተኛ ደረጃ፣ በጣም የጋለውን ሩሲያ ውስጥ የተካኼደውን ክርክር ካቀረብን በኋላ ቪ ጅ የቢሊንስኪን አስታራቂ ሐሳብ፣ ማለትም፣ ሥነጥበብ ይዛ የምትቀርበው ጉዳይ ምንም ኾነ ምን ሥራው የነገረውበት መስፈርትን እስካሟላ ድረስ ተቀባይነት ይኖረዋል የሚለውን ሐሳብ፣ “የዐሥራዘጠነኛው መቶ ክፍለ-ዘመን መፍትሔ” ብለን እናሳያለን። በሦስተኛ ደረጃ፣ “የኻያኛው መቶ ክፍለ-ዘመን መልስ” ብለን የ ሲ. ኤስ. ሉዊስ እና የአልቤር ካሙ'ን ምላሽ እንመረምራለን። የኻያኛው መቶ ክፍለ-ዘመን አተያይ ከዐሥራዘጠነኛው መቶ ክፍለ-ዘመን አመለካከት ጋር አንድነት እና ልዩነት እንዳላቸውም እንመረምራለን።

ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ደስታ
Copyright (c) 2025
2025-04-10
2025-04-10
33 2
30
61

የአርጐባ ብሔረሰብ የለቅሶ ሥነ ስርዓት ትንተና፦ ክዋኔው፣ መዋቅሩ፣ ትዕምርቱና ፋይዳው
https://ejol.aau.edu.et/index.php/JAELC/article/view/11607

የጥናቱ ዋና ዓላማ የአርጐባ ብሔረሰብን የለቅሶ ሥነ ስርዓት ክዋኔ፣ መዋቅር፣ ትዕምርትና ፋይዳ መተንተን ነው። የአርጐባ ብሔረሰብ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሐረሪና በአፋር ክልሎች ውስጥ የሚኖር ሲሆን (አህመድ 1999፡ 161) የዚህ ጥናት ትኩረት የአፋሩ አርጐባ ነው። ሥነ ስርዓት "አንድን ድርጊት በተመለከተ የተለመደ ስርኣትን ወይም ደንብን ተከትሎ የሚሄድ ክንውን" (የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዳሚ 2ዐዐ6: 138) ነው። ክዋኔ የተግባቦት ስልት (Bauman 1975: 293)፣ መዋቅር የነገሮች ንዑሳን ክፍሎችና እርስ በርስ ያላቸው ግንኙነት (Storey 128)፣ ትዕምርት ሀሳብን የሚያስተላልፍ ቁስ፣ እንቅስቃሴና ግንኙነት (Geertz qtd.[5] in Turner 1997: 145) ሲሆን ፋይዳ ሥነ ስርዓቱ ለከዋኙ ማኀበረሰብ የሚሰጠው ጠቀሜታ ነው። በጥናቱ የቀደምት ጥናቶች ንባብና የመስክ ስራ ተከናውኗል። በመስክ መረጃ የተሰበሰበባቸው ዘዴዎች ምልከታ፣ ቃለመጠይቅና ቡድን ተኮር ውይይት ሲሆኑ ዓላማ ተኮርና ጠቋሚ የናሙና ዘዴዎች ጥቅም ላይ ውለዋል። መረጃን ለመተንተን ኢትኖግራፊ የጥናት ሞዴል ጥቅም ላይ ውሏል። የጥናቱ ግኝት የብሔረሰቡ የለቅሶ ሥነ ስርዓት ክዋኔ በመለየት፣ ሽግግርና መቀላቀል ሶስት ደረጃዎች ሊከፈል የሚችል መሆኑን፣ ድርጊታዊና (በቀኝ ማስተኛት፣ ጥልፍ መተርተር፣ ሽቶና ውሀ ማርከፍከፍ፣ ቅጠል መጐዝጐዝ፣ የሟችን ሚስት ቅቤ መቀባትና አዲስ ቀሚስ ማልበስ፣ ቆዳን በጠዋት ውሀ አርከፍክፎ ማጠፍ፣ በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ) ቁሳዊ (ውሀ፣ ቆዳ) ትዕምርቶች መኖራቸውን፣ ሥነ ስርዓቱ ተግባቦታዊና ማኀበራዊ (ለቅሶ መድረስ)፣ ኢኰኖሚያዊና (ሀፈሻ) ሥነ ልቡናዊ (በጋራ ማልቀስና ሶደቃ) ፋይዳዎች ያሉት መሆኑን አሳይቷል። ሀፈሻን ከዘመናዊ የመረዳጃ ተቋማት ጋር ማስተሳሰር ለቀጣይነቱ አስተዋጽኦ ያደርጋል፤ ዚያራ[6]ም በጥልቀት ቢጠና መልካም ነው።

ቁልፍ ቃላት፣ [አርጐባ፣ ለቅሶ፣ ሥነ ስርዓት፣ ክዋኔ]

እታገኘሁ አስረስ[1]፣ ዘሪሁን አስፋው (ተባባሪ ኘሮፌሰር)[2]፣ የኔዓለም አረዶ (ዶ/ር)[3]፣ መሐመድ አሊ (ዶ/ር)[4]
Copyright (c) 2025
2025-04-10
2025-04-10
33 2
62
91

Acquisition of Dialect in Oromo Children: A Phonological Analysis
https://ejol.aau.edu.et/index.php/JAELC/article/view/11600

This study investigates the variations of Oromo phonological development in typically developing four-year old monolingual children in Ethiopia, where a broad range of Oromo dialects exist. The children’s phonological development was measured using picture naming test. Speech samples were collected from 70 children from Arero, Dera, Baate and Kamisee. These subjects formed two groups: Oromos who speak Oromo and live outside of Oromia (Baate & Kamisee), and Oromos who speak Oromo and live in Oromia (Arero & Dera). Independent and relational analyses were conducted to obtain phonological inventories as well as phonological patterns from children in Arero and Baate. Children across sites demonstrated similar sizes of consonant inventories, suggesting a common progression of sound acquisition in all dialectal areas, with few variations that impacted namely /kˈ/, /ʤ/, /s/, and /r/. The absence of statistical differences in children’s consonant accuracy across dialectal areas could be attributed to the minimal dialectal variation of adult Oromo. An unusual observation arising from the phonological pattern analysis was children acquiring the language deleted the first unstressed cluster and repeated and geminated the second stressed cluster. The phonological pattern analysis also provided insight on possible dialectal variations in Arero and Baate including gliding and stopping errors.

Keywords: [Acquisition of dialect variations, Cushitic, Oromo, Phonological development,]

Samson Fantu[1] and Ronny Meyer[2]
Copyright (c) 2025
2025-04-10
2025-04-10
33 2
92
121

የጊዜ እሳቤ በተመረጡ የአማርኛ ግጥሞች
https://ejol.aau.edu.et/index.php/JAELC/article/view/11583

አጠቃሎ

ጊዜ በአማርኛ ግጥሞች ውስጥ ተደጋግመው ከሚነሱ ጭብጦች ውስጥ አንዱ ነው። የዚህ መጣጥፍ ዓላማ የተመረጡትን ግጥሞች የጊዜ እሳቤ መተንተን ነው። ይህንንም ከግብ ለማድረስ በጊዜ ፍልስፍና ውስጥ ዋና የሆኑት የአሁናዊነት እና የዘላለማዊነት ንድፈ ሐሳቦች ከጊዜ ቀስት ጋር በመተባበር ጽንሰ ሐሳባዊ ማዕቀፉን አበጅተዋል። በዚህም በመታገዝ የቴክስት ትንተና ተካሂዷል። ዓላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ብልሃትን በመከተል ሦስት ግጥሞች ለጥናት የተመረጡ ሲሆን እነርሱም የሥዩም ተፈራ (1999) “የማንኖራት ቅጽበት”፣ የሱራፌል ለገሠ (1998) “አሁን ወደፊት ነው” እና የተሾመ ገ/ሥላሴ (1995) “የጊዜ ቅንጣቶች”፣ ናቸው። ሦስቱ ግጥሞች ከሌሎች ግጥሞች ተለይተው የተመረጡበት ምክንያት በአካላይ ዓመቱ ውስጥ በስፋት የተነሳውን ደቂቅ የሆነውን የጊዜ እሳቤ ለማሳያነት ምቹና ብቁ በመሆናቸው ነው። በትንታኔ ወቅት እንደታየው በሦስቱም ግጥሞች ውስጥ የተነሳው የጊዜ ጽንሰ ሐሳብ እጅግ ደቂቅ የሆኑትንና የሰው ልጅም ስለማያስተውላቸው ቅጽበታት ነው። እነዚህ ቅጽበታት በሰው ልጅ ግንዛቤ ኖራቸውም አልኖራቸውም በፍጥነት እያለፉ የህላዌን ክሱትነት የሚያስቀጥሉ ሲሆኑ ጊዜም የተገነባባቸው አላባውያን ናቸው። ከትንታኔው ተነስቶ ማጠቃለል እንደሚቻለው እንደ ግጥሞቹ እይታ ጊዜ ነባራዊና አላፊ የሆነ የለውጥ ኃይል ነው። ለውጡ በአላፊ፣ አሁናዊ እና መጻኢ ቅጽ የሚታወቅ ቢሆንም የቅጾቹ ባሕርይ እንደየ ኹነቶቹ ተለዋዋጭ ነው።

ቁልፍ ቃላት

[የጊዜ ፍልስፍና፣ የጊዜ ቅጽ፣ ኹነት]

ሰላማዊት በየነ
Copyright (c) 2025
2025-04-10
2025-04-10
33 2
122
137

ምስለ ዐባይ በአማርኛ ሥነ ጽሑፍ፣ 1957-2008 ዓ/ም
https://ejol.aau.edu.et/index.php/JAELC/article/view/11608

ዐባይ ለእልፍ ዓመታት ለጥንታዊዋ ግብፅ ሥልጣኔ ምሰሶዋ የነበረውን ያህል ዛሬም ለብዙ ሚሊዮን ግብፃውያን የሕልውናቸው ዋልታ ነው። ጥቁር ዐባይ ከነጭ ዐባይ ጋራ ካርቱም ላይ ከተቀላቀለ በኋላ የሱዳንን በረሓ አቋርጦ በግብፅ ውስጥ ለመጠጥ፣ ለመስኖ እርሻ፣ ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ ለኢንዱስትሪ ፍጆታ፣ ለጀልባ ትራንስፖርትና ለቱሪዝም መስሕብ ያገለግላል። ከግብፅ ጋራ ባይመጣጠንም፣ ለሱዳንም ዘርፈ ብዙ ጥቅም ይሰጣል። ዐባይ በየዓመቱ ብዙ ቢልዮን ኩብ ጫማ ለም ዐፈር ከኢትዮጵያ እየጠራረገ ለሁለቱ የጎረቤት አገሮች እርሻ ቢያቀርብም ለመነጨበት አገር የነሱን ቅንጣት ያህል ጥቅም ሳይሰጥ ኖሯል። ኢትዮጵያ ለናይል ወንዝ 86% የሚኾነውን ውሃ ብታበረክትም እስካሁን የምትጠቀምበት የዐባይ ውሃ መጠን ከ1% እንደማይበልጥ ይገመታል። አገሪቱ ከዐባይ ወንዝ ፍትሓዊ ተጠቃሚ እንዳትኾን ሲከላከሉ የኖሩት የታችኛው ተፋሰስ ጎረቤቶቿ የሕዳሴው ግድብ ግንባታ መጀመሩ ሲታወቅ ምላሻቸው ከምንጊዜውም የከረረ ባላንጣነት መኾኑ ወንዙ ሦስቱን አገሮች በበጎም ኾነ በክፉ ምን ያህል እንዳስተሳሰረ አንዱ ማሳያ ነው። ዐባይ በዘርፈ ብዙ ጥቅሙ በሦስቱ አገሮች ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊና ሃይማኖታዊ ግንኙነት ላይ የታሪክ አሻራውን ትቷል፤ በሕዝቦቹ ሥነ ልቦናና ባህል ላይም ተጽዕኖ አሳድሯል። በኢትዮጵያ የዚህ ተጽዕኖ አንዱ መገለጫ ከሌሎች የአገሪቱ ወንዞች የበለጠ ለዐባይ በሥነ ጽሑፏ ውስጥ የተሰጠው ሰፊ ሽፋን ነው። ስለኾነም የዚህ ጥናት ቀዳሚ ዓላማ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እስከ ኢሕአዴግ ዘመነ መንግሥት ለንባብ በበቁት የአማርኛ የፈጠራ ድርሰቶች ለዐባይ የተሰጠውን ምስል እና ድርሰቶቹ በዐባይ ዙርያ የሚያጠነጥኑትን ዋና ዋና ጭብጦች መቃኘት ነው። ኹለተኛው ዓላማ ከዚሁ ጋራ በተያያዘ ዐባይ በድርሰቶቹ ውስጥ የተሰጠውን ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሚና፣ እንዲሁም በጊዜ ኺደት ከነዚህ አንጻር የተከሠተን የለውጥ አዝማሚያ ለይቶ ማሳየት ነው። እግረ መንገዱንም ከዐባይ ጋር በተዛመደ በዚሁ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ሱዳንና ግብፅ የተሣሉበትን ዕይታ ይዳስሳል። ጥናቱ የተከተለው ዘዴ ምንባባዊ የይዘት ትንተና ነው። በየዘመኑ ድርሰቶች ዋና ዋና የዐባይ ምስሎችንና ጭብጦችን መዳሰስ ሰፊ የጥናት አድማስን ግድ ስለሚል ለዚህ ዋቢ የኾኑትን የፈጠራ ድርሰቶች ማግኘት የተቻለውን በጥናቱ ለማካተት ተሞክሯል። ለጭብጦቹ ዳራ የኾኑ ሌሎች ዐባይ-ነክ ምርምራዊ ሥራዎችንም እንደ አስፈላጊነቱ በማጣቀሻነት ጥናቱ ተጠቅሟል።

ቁልፍ ቃላት፦ [ዐባይ፣ ምስለ ዐባይ፣ ዐባይና ጥንታዊ ሥልጣኔ፣ ዐባይና ባህል፣ ድኀነትና ኋላቀርነት፣ዐባይና ልማት፣ ሕዳሴ ግድብ፣ ግብፅ፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ የውሃ ፖለቲካ]

ታዬ አሰፋ
Copyright (c) 2025
2025-04-10
2025-04-10
33 2
138
192