ዕርቀሰላም፡- የቱለማ ኦሮሞ ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ስልት መቋጫ

Authors

  • ገናናው ከተማ Kotebe Education University
  • ታደሰ በሪሶ Addis Ababa University

Keywords:

ኦሮሞ፣ የገዳ ሥርዓት፣ ዕርቀሰላም፣ ቦኩ፣ ከለቻ

Abstract

የዚህ ጥናት ዓብይ ዓላማ የቱለማ ኦሮሞን ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ስልት መተንተን ነው፡፡ በዚህ መሰሉ የሰላም ፍኖት አቀራረብ እራሱን ችሎ የተሰራ ጥናት አላገኘንም፡፡ ይኸውም አነሳሽ ምክንያት ሆኗል፡፡ ለጥናቱ ስኬት አስፈላጊ የሆኑ ቀዳማይ እና ካልዓይ የሆኑ መረጃዎች ተሰብስበው ተተንትነዋል፡፡ ቀዳማይ መረጃዎቹ በምልከታ፣ ቃለመጠይቅ እና የቡድን ውይይትን የተሰበሰቡ ናቸው፡፡ ጥናቱ ዓይነታዊ የምርምር ዘዴን ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን በገላጭ ስልት የተቃኘ ነው፡፡ የተጠቀሱትን ስነዘዴዎች ለጥናቱ መመልከቻነት ከመረጥናቸው ፅንሰ ሃሳባዊ እና ንድፈ ሃሳባዊ ማዕቀፎች ጋር በማቀናጀት የጥናታችንን ዓላማ ከግብ አድርሰናል፡፡ በዚሁ መሠረት በኅብረተሰቡ ዘንድ ዕርቅ እና ሰላም (Araara fi naga’a) ለማስፈን ባህላዊ የሽምግልና፣ ሸነቻ፣ ቂጤ (Qixxee) እና የጉማ ሥርዓት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው በዚህ ጥናት ተመላክቷል፡፡ እነዚህን የግጭት አፈታት ስልቶች ውጤታማ ለማድረግ  እንደ “ቦኩ፣ ከለቻ እና ጫጩ” ያሉ የከበሩ ንዋያት የማይተካ ሚና አላቸው፡፡ በተለይም የጉማ ሥርዓትን ካለ ከለቻ እና ጫጩ ማሰብ አስቸጋሪ ነው፡፡ የሀገር በቀል እውቀት ውጤት የሆኑት እነዚህ የኦሮሞ ባህላዊ የግጭት አፈታት ስልቶች ዋና ማጠንጠኛቸው እውነት፣ ግባቸውም ዘላቂ ሰላምን ማስፈን ስለሆነ ከዕርቅ በኋላ የጥላቻ እና የበቀል ስሜትን አጥፍቶ በፍቅር እና በሰላም አብሮ ለመኖር ጉልህ ድርሻ እንዳላቸውም የጥናቱ ማጠቃለያ ያሳያል፡፡ ከጥናቱ የመነጨ ይሁንታም ቀርቧል፡፡

Downloads

Published

2024-02-28