የዘመናዊ ሥነ ጽሑፍ መገለጫዎች በጥንታዊ ድርሳናት ውስጥ - እንዚራ ስብሐት እንደ ማሳያ

Authors

  • ተስፉ አስማረ ሞላ Wollo University

Keywords:

ጥንታዊ ጽሑፍ፣ ግእዝ፣ ድርሳን፣ ቅርስ፣ ግጥም፣ ሥንኝ ፤ ዘይቤ ፤ ዕሴት።

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ውስጥ ከደረሷቸው መጻሕፍት መካከል አንዱ ነው ተብሎ በሚታመነው ‘እንዚራ ስብሐት’ ላይ የይዘት ትንተና ማካሄድ ነው። እንዚራ ስብሐት የተዘጋጀው ድንግል ማርያምን ለማወደስ ሲሆን፤ በጠቅላላው በሁለት መቶ ሁለት የግእዝ ፊደላት ተረፎችንም ጨምሮ በቅደም ተከተላቸው የተደረሰ ሀገርኛ የሆነ ግጥማዊ የሥነ ጽሑፍ ሀብት ነው። ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ እንደደረሱት የሚታመነው እንዚራ ስብሐት የተባለው መጽሐፋቸው
በዘመኑ የነበረውን የሥነ ጽሑፍ ዕድገት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። በእንዚራ ስብሐት ላይ የይዘት ትንተና ለማከናወን አንድ ጥንታዊ የብራና መጽሐፍ እና ሁለት የብራና ቅጅ የሆኑ የታተሙ መጻሕፍት ጥቅም ላይ ውለዋል። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እና የጠራ ሐሳብ ለመያዝ ቃለ መጠይቅ በተጨማሪ የመረጃ ምንጭነት ጥቅም ላይ ውሏል። በእንዚራ ስብሐት ይዘት ውስጥ እንደሚስተዋለው ደራሲው ራስን ከሐሳብ ስርቆሽ (Plagiarism) ለመታደግ የሚበጁ ማምለጫ ስልቶችን፣ ማለትም ቀጥተኛ ጥቅስ፣ ጭምቅ ሐሳብና ግለ ገለጻን
ተጠቅሟል። የአንድ ጸሐፊ የአገላለጽ ብቃት እና የጽሑፉ ውበት ዋነኛ መገለጫ የሆኑ የዘይቤ ዓይነቶች በእንዚራ ስብሐት ውስጥ ጥቅም ላይ ውለዋል። በመሆኑም በግጥማዊ ድርሰቱ ውስጥ ዐሥር የዘይቤ ዓይነቶችን ለመለየት ተችሏል። ከዚህም በተጨማሪ በእንዚራ ስብሐት ውስጥ የሚገኙት ዕሴቶችም ተለይተው ከማሳያ ጋር ተተንትነዋል። በማጠቃለያም እንዚራ ስብሐት በዘመኑ (በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን) የግእዝ ሥነ ጽሑፍ ብቃት ምን ያህል ደረጃ ላይ ደርሶ እንደ ነበር ጥሩ ማሳያ ስለሚሆን ለተጨማሪ ምርምር የሚጋብዝ ምንጭ ሊሆን እንደሚችል ጥናቱ ጠቁሟል።

Downloads

Published

2023-11-16