የአርጐባ ብሔረሰብ የወሊድ ስነ ስርዓት ክዋኔ ትንተና

An Analysis of the Birth Rite of the Argobba Ethnic Group

Authors

  • Etagegnehu Asres
  • Zerihun Asfaw Addis Ababa University
  • Yeniealem Aredo Addis Ababa University
  • Mohammad Ali Addis Ababa University

Keywords:

አርጐባ፣ ወሊድ፣ ስነ ስርዓት፣ ክዋኔ, Argobba, Birth, Ritual, Performance, Rite

Abstract

ይህ ጥናት የአርጐባ ብሔረሰብን የወሊድ ስነ ስርዓት ክዋኔ የመተንተን ዋና ዓላማ ያለው ነው፡፡ የጥናቱን ዓላማ ለማሳካት ካልዓይና ቀዳማይ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ ካልዓይ መረጃ ቀደም ብለው የተሰሩ የጽሁፍ ምንጮችን በማንበብ የተገኘ ሲሆን ቀዳማይ መረጃ ለማግኘት የመስክ ስራ ተከናውኗል፡፡ በመስክ መረጃ የተሰበሰበባቸው ዘዴዎች ምልከታ፣ ቃለመጠይቅና ቡድን ተኮር ውይይት ሲሆኑ መረጃ ሰጪዎች በዓላማ ተኮርና ጠቋሚ የንሞና ዘዴዎች ተመርጠዋል፡፡ የተሰበሰበው መረጃ ከዓይነታዊ የመረጃ መተንተኛ ዘዴ ውስጥ የኢትኖግራፊ ጥናት ሞዴልን በመጠቀም ተተንትኗል፡፡ የጥናቱ ግኝት እንደሚያሳየው የአርጐባ ብሔረሰብ የወሊድ ስነ ስርዓት ክዋኔ በሶስት ደረጃዎች ሊከፈል የሚችል ነው፡፡ በክዋኔው ስነቃል (ዱዓዎች፣ ዝኪሮች፣ መማፀኛዎች፣ መልካም ምኞትን መግለጫዎች፣ ምሳሌያዊ አነጋገሮች፣ ዝየራዎች)፣ ቁሳዊ ባህል (ባህላዊ ምግብና መጠጥ፣ አልባሳት፣ የማዋለጃ ቁሳቁሶች፣ የእንግዴ ልጅ መቅበሪያ ቁስ)፣ ማህበራዊ ልማድ (እምነቶች፣ ባህላዊ ሕክምና፣ ስም አወጣጥ፣ የፀጉር አሰራር፣ ጭስ መሞቅ) ፎክሎሮች ተለይተዋል፡፡ ቃላዊ (የዱዓ ቃላት)፣ ቁሳዊና (ገንፎ) ድርጊታዊ (ጣትን በገበታ ዙሪያ ማድረግ፣ ገበታን ከፍ ማድረግ፣ ድፍን ቅል አጥቦና አልጋ ላይ ማድረግ፣ የወላድ ቡና መጨበጥና ቡናን ምጣድ ላይ አድርጐ መጠበቅ) ትዕምርቶች ተለይተው ፍቺዎቻቸው ቀርበዋል፡፡ ስነ ስርዓቱ ማህበራዊ፣ ስነ ልቡናዊና፣ እሴቶችን የመትከል ፋይዳዎች አሉት፡፡ ዘመናዊ የህክምና ተቋማት ማዋለጃዎቸቸውን በባህሉ መሰረት ማስተካከል ቢችሉ፤ የነፍሰጡር የምግብ ክልክሎች ነፍሰጡር ልታገኝ የሚገባውን ንጥረ ነገር የሚያሳጣ መሆን አለመሆኑና አንዳንድ የወሊድ ክዋኔዎች (ለምሳሌ፣ መነቅነቅ፣ ሆድ ማሸት) ከጤና አንፃር የሚያስከትሏቸው የጤና ጉዳቶች ካሉ በወረዳው የጤና ጽ/ቤት ጥናት ተከናውኖ ጉዳቱ ቢለይ ጥሩ ነው፡፡ 

This study has the main objective of analyzing the performance of the birth rite of the Argobba ethnic group. Secondary and primary data were collected to achieve the objective of the study. Secondary data was obtained by reading earlier written sources, and fieldwork was conducted to obtain primary data. The methods of field data collection are observation, interview, and focus group discussion, and informants were selected by purposive and snowball sampling methods. The collected data were analyzed using an ethnographic research model from a qualitative data analysis method. According to the findings of the study, the performance of the Argobba birth rite can be divided into three stages. In the performance, oral traditions (prayers, Zəkiroč, supplications, expressions of good wishes), material culture (traditional food and drink, clothing, birthing materials, placenta burial material), and social custom (beliefs, Ziyarawoč, traditional medicine, naming, hairstyles, getting smocked Azəgaro and Wäyəba smokes) folklores have been found. Verbal (words of prayer), material (porridge), and action (putting fingers around a plate, raising a plate, washing a calabash and putting it on a bed, holding coffee and keeping it on a pan) symbols and their interpretations are presented. The rite has social, psychological, and justification benefits. It would be good if modern medical institutions could adjust their delivery rooms according to the tradition if the district health office conducts a study to determine whether or not pregnant food habits are depriving the pregnant of the nutrients they should be getting and if there are any health risks caused by certain performances (e.g., shaking, belly rubs) in terms of health.

Downloads

Published

2025-01-11