በሶስተኛና አራተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻህፍት የስርዓተጾታ ፍትሃዊነት ፍተሻ

  • አራጋው ሺባባው

Abstract

ይህ ጥናት በሶስተኛና በአራተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻህፍት የስርዓተጾታ ፍትሃዊነት ምን እንደሚመስሉ
መመርመር ላይ ያተኮረ ነው። ለዚህም ሁለቱ መማሪያ መጻህፍት በዓላማ ተኮር ስልት ተመርጠዋል። መረጃዎችም በሰነድ ፍተሻ
ስልት ተሰብስበዋል። የተሰበሰቡ መረጃዎም በካይ ካሬ፣ በድግግሞሽ ቆጠራ፣በሬሾና በመቶኛ ተተንትነዋል። ከተገኘው ትንተና
እንደተስተዋለውም፣ ሴቶች በስም የቀረቡበት የድግግሞሽ መጠን 66(54.09%) ሲሆን ወንዶች የቀረቡበት የድግግሞሽ መጠን
ደግሞ 56(45.9%) ነው። የካይ ካሬ ፍተሻ እንዳሳየውም p>0.05 ሆኗል። የጉልህነት ውጤቱም .157 ሆኗል። ይህም በሁለቱ
ጾታዎች መካከል የጎላ ልዩነት እንደሌለ የሚያሳይ ነው። የሴት ወንድ የስም ድግግሞሽ ሬሾ/ጥምርታ/ ሲታይ ደግሞ 1.12 ሴት
ለ1 ወንድ ነው፡፡ ከዚህ አንጻርም በጾታ ድግግሞሽ የጎላ ልዩነት አልተስተዋለበትም። የሁለቱ ጾታዎች ማህበራዊ ሚና ሲታይ
መጻህፍቱ ሴቶች ዋናዋና በሚባል ደረጃ በብዛት የቀረቡበት ሚና የለም። ከተሳተፉባቸው ሚናዎች መካከል ግን ሴቶችን መግረዝ፣
ዳቦ መግዛት፣ ዳቦ መሸጥ፣ ልጅ መንከባከብ፣ የህክምና ምክር መስጠት፣ መብት መጠየቅ፣ በሽተኛ መንከባከብ ይገኙበታል።
ኳስ መጫዎት፣ በሽተኛ ተሸካሚ መሆን፣ ሩጫ ደጋፊ መሆን፣ ሳርቤት መክደን፣ፖሊስና ሹፌር ሆኖ መስራት ወንዶች በብዛት
የተሳተፉባቸው ዋናዋና ሚናዎች ናቸው። ከዚህ አንጻር ሚና ላይ የፍትሃዊነት ችግር አለ ማለት ይቻላል፡፡ ውክልናን በተመለከተ
ደግሞ በሁለቱም ጾታዎች ሴት ወይም ወንድ ሲባል ትዝ በሚል መንገድ የተስተዋሉ ውክልናዎች የሉም ማለት ይቻላል፡፡
ሳይደጋገሙ የቀረቡ ውክልናዎች ሲታዩ ግን ወንዶች በአንጻራዊነት በተሻሉ ነገሮች የተወከሉ ሲሆን ሴቶች ደግሞ ዝቅ ባሉ ነገሮች
ተወክለው ቀርበዋል። ይህም ከውክልና አንጻር ክፍተት መኖሩን የሚያሳይ ነው። በመሆኑም ወደፊት የስርዓተትምህርት አዘጋጆች
በሚያዘጋጇቸው መጻህፍት ጥንካሬዎቹን በማስቀጠል በድክመቶቹ በኩል ማሻሻያ ቢያደርጉ መልካም ነው።

References

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት-ቢሮ። (2002)። የስርዓተትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዋና የስራ
ሂደት ተግባራት ማስፈጸሚያ ስትራተጂና ልዩልዩ መመሪያዎች። የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት
ትምህርት-ቢሮ፡ ባህርዳር።
Akam ,P. E. (2009). The Effect of Gender Division of Labour on the Education of Rural
School Children. The case of two primary schools in Medig,Cameroon. Depart
ment of Sociology and Human Geography. (Master thesis). Universiteteti Oslo.
Candida, M. et al. (1999). A Guide to Geneder- Analysis Frameworks. UK: An Oxfam
Publication.
Carole B.(2009). Promoting Gender Equality through Textbooks: A methodological guide.
Published by the United Nations Educational, Scientific and Cultural
Organization. France.
Cornwall, A., Harrison, E. & Whitehead, A. (2007). Gender Myths and Feminist Fables:
The struggle for interpretive power in gender and development. England:
Blackwell publishing.
Cranny-Francis, A. et al (2003). Gender Studies Terms and Debates. New York
Basingstoke: Palgrave Macmillan. Palgrave Macmillan publisher.
Hornby,A.S. (1989). Oxford Advanced Learner’s Dictionary. 4th Edition. UK: Oxford Univ
Press. https://www. indexm undi.com/ethiopia/millennium-development-goals.
html (16/ 9/2010)
Jackie,F.K.Lee.(2002). Geneder represenetation in HongKong English Text Books. Piter
Collins: The University of New South Wales.
Kevane, M. (2004). Women and Development in Africa: How Gender Works. Boulder
London: Lynne Rienner Publishers.
Taylor,F. (2003). Contenet analysis and Geneder Sterotypes in Children’s Books.
Published
2018-07-17
How to Cite
ሺባባው, አራጋው. በሶስተኛና አራተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻህፍት የስርዓተጾታ ፍትሃዊነት ፍተሻ. The Ethiopian Renaissance Journal of Social Science and Humanities, [S.l.], v. 5, n. 1, p. 87 - 93, july 2018. ISSN 2409-6385. Available at: <http://ejol.aau.edu.et/index.php/ERJSSH/article/view/1229>. Date accessed: 24 jan. 2020.
Please advise your journal citation style before using the above citation format, you can also find your citation style from citation formats listed down.