ሒሳዊ ቅኝት÷ በሰሎሞን ተሾመ፣ ፎክሎር፡ ምንነቱና የጥናቱ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ገዛኸኝ ጸጋው

  • ገዛኸኝ ጸጋው በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍና ፎክሎር መምህር

Abstract

ይህ ሒሳዊ ቅኝት፣ የ ፎክሎር፡ ምንነቱና የጥናቱ የትኩረት አቅጣጫ (2007 ዓ.ም.) መጽሐፍን ይዘትና ቅርጽ በተጠኑ መለኪያዎች መዝኖ፣ ዋና ዋና የሚባሉ ውስንነቶቹን ለማመላከትና ማረሚያ ነጥቦችን ለመጠቆም ሞክሯል፡፡ ጥናቱ፣ ከሙያዊ መጽሐፍ ግምገማ ጋራ ተያይዞ ተመራጭ እንደሆኑ የታመነባቸው፣ ሦስት በይነ ዲሲፕሊናዊ ማንጸሪያዎችን (perspectives) ተጠቅሞ፣ ከአካዳሚያዊ ዐውዶች ጋራ እያናበበ ተንትኗል፡፡ በሂደቱም መጽሐፉ፣ በፎክሎር መሠረታዊ ፅንሰ ሐሳቦችና ንድፈ ሐሳቦች ላይ መፋለሶች እንደተከሠቱበት፤ ያጣቀሳቸው ማስረጃዎች፣ መረጃዎችና የመረጃ ምንጮች (መጽሐፉንም ሙያዉንም በሚፈታተኑበት ደረጃ) ትክክለኝነትና ተገቢነት እንደሚጎላቸው፣ እንዲሁም፤ የሙያዊ ቃላት መዘበራረቆች፣ የትርጉም ስሕተቶችና የሰዋስው ግድፈቶች የመጽሐፉን የቋንቋ አጠቃቀም ሁኔታ እንደሚያደነቃቅፉበት በበቂ አስረጂዎች ተረጋግጧል፡፡ ጥናቱ፣ ለሁሉም የመጽሐፉ ደካማ ጎኖች ማመሳከሪያና ማረሚያ የሚሆኑ ማስረጃዎችንና የመረጃ ምንጮችን ስለሚጠቁም፣ መጽሐፉን በማስተማሪያነትና በማጣቀሻነት በሚገለገሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተማሪዎች መካከል፣ አካዳሚያዊ ውይይቶች እንዲደረጉ፣ መጽሐፉም ሕጸጾቹን አርሞ የሚቀርብበት መንገድ እንዲመቻች መልካም አጋጣሚዎችን ለመጠቆም ሞክሯል፡፡

Downloads

Download data is not yet available.

References

ሰይፉ መታፈሪያ፤ 1993 (እ.ኤ.አ.)፤ “የፎክሎር መዝገበ ቃላት ጥንቀራ ቅድመ ዝግጅት፤” የኢትዮጵያ ጥናት መጽሔት፤ ቅጽ 26፣ ቁጥር 1 ጁን 1993፤ ገጽ፡ 73-116፡፡
………፤1973፤ “ሥነ /ኪነተ ቃል በኢትዮጵያ፤” (“ትውፊት” በሚል ርእስ፣ ከሐምሌ 1-3/ 1973 ዓ.ም. በተዘጋጀ ሴሚናር ላይ የቀረበ)፤ አ.አ.ዩ.፤ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ ክፍለ ትምህርት፣ ገጽ፡ 1-50፡፡
ሳሙኤል እንዳለ፤ 1982፤ “ሥነ ቃል ነክ ስያሜዎች አጠቃቀምና ችግራቸው፤” በአ.አ.ዩ.፤ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ ክፍለ ትምህርት ለዲግሪ ማሟያ የቀረበ፡፡
ባሕሩ ዘውዴ፤ 2003፤ “መግቢያ ፩፤” የነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ ሥራዎች፤ አዲስ አበባ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ፡፡
More inside the PDF
Published
2018-01-01
How to Cite
ጸጋው, ገዛኸኝ. ሒሳዊ ቅኝት÷ በሰሎሞን ተሾመ፣ ፎክሎር፡ ምንነቱና የጥናቱ የትኩረት አቅጣጫ ላይ ገዛኸኝ ጸጋው. Ethiopian Journal of Languages and Literature, [S.l.], v. 14, n. 1, p. 33 - 58, jan. 2018. Available at: <http://ejol.aau.edu.et/index.php/EJOLL/article/view/2008>. Date accessed: 27 oct. 2020.
Please advise your journal citation style before using the above citation format, you can also find your citation style from citation formats listed down.