የሰብአዊነት አሣሣል በዐፄ ሱስንዮስ ዜና መዋዕል እና በበዓሉ ግርማ የቀይ ኮከብ ጥሪ ውስጥ

  • ታዬ አሰፋ

Abstract

የአማርኛ ዘመናዊ ልቦለድ እድገት ከአፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ ልብ ወለድ ታሪክ (ጦብያ) በ1900190019001900 ዓ/ም መታተም በኋላ ጎላ ያለ የጭብጥም የቅርጽም ለውጥ አስመዝግቧል፡፡ በርካታዎቹ የዘመናዊነት ገጽታዎቹም የዚህን የሥነ ጽሑፍ ዘውግ አታቾች ትኩረት በተለያየ ደረጃ ስበዋል፡፡ ሆኖም፣ ለአማርኛው ልቦለድ የግእዙ ሥነ ጽሑፍ መሠረትነት ወይም ይህ የልቦለድ ዘውግ በእድገት ግሥጋሴውም ላይ ቢሆን ከግእዙ ጋር በምን ሁኔታ እንደሚወራረስ ለማሳየት የሚገባውን ያህል በተመራማሪዎች አልተፈተሸም፡፡ ይህ ጽሑፍ ለአብነት የዐፄ ሱስንዮስን ዜና መዋዕል (ከግእዝ ወደ አማርኛ የተተረጎመ) ከበዓሉ ግርማ የቀይ ኮከብ ጥሪ ጋር በማነጻጸር ከሥነ ምግባራዊ ሰብዓዊነት ጭብጥ አተራረክ አንጻር ሁለቱ ያላቸውን ተመሳስሎና ልዩነት ለማሳየት ይሞክራል፡፡ ሁለቱን ድርሰቶች ለማነጻጸር መንደርደሪያው ሁለቱም ትርክ መሆናቸው፣ የሚሥሉት እውነታ በምናብ የተዋዛ መሆኑ፣ ታሪካቸው በተወሰነ ደረጃ በተመሳሳይ ፖለቲካዊ መርሖች የተቃኘ መሆኑና የሁለቱም ደራስያን የፖለቲካ ሹመኞች መሆናቸው ነው፡፡ ጽሑፉ ለአምባገነን አገዛዝ የቅርብ ባለሟል የሆነ ደራሲ ድርሰቱን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ማዋሉ ከጥንት የተወረሰ የድርሰት ባህል መሆኑን በአንድ በኩል ቢያረጋግጥም በሌላ በኩል ግን የኅሊና ሙግት ያለበት ደራሲ የፕሮፓጋንዳውን ማርከሻ በተዘዋዋሪ ለአንባቢው የሚያቀርብበት ሰምና ወርቅ ቅኔ መሰል የአተራረክ ስልት እንዳለውም ከዜና መዋዕሉ ማስረጃዎችን በመጠቃቀስ ያሳያል፡፡

Downloads

Download data is not yet available.

References

መስፍን ሀብተ ማርያም፡፡ 1972 ዓ/ም፡፡ ሥነ ጽሑፍ ከአብዮት ፍንዳታ ወዲህ፤ የቀይ ኮከብ ጥሪ (ግምገማ)፤ የካቲት፤ 3ኛ ዓመት፣ ቁ. 5፣ ገጽ 26 -27 ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ፤ 2000 ዓ/ም፤ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት፤ አዲስ አበባ፤ የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፡፡
በዓሉ ግርማ፤1972 ዓ/ም፤ የቀይ ኮከብ ጥሪ፤ አዲስ አበባ፤ የኢትዮጵያ መጻሕፍት ድርጅት፡፡
_____ ፤ 1975197519751975 ዓ/ም፤ ኦሮማይ፤ አዲስ አበባ፤ ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት፡፡
ተሰማ ሀብተሚካኤል፤ 2002200220022002 ዓ/ም፤ ከሳቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት፤ አዲስ አበባ፡፡
ተክለ ኢየሱስ ዋቅጅራ (አለቃ)፤ 2002 ዓ/ም፤ የኢትዮጵያ ታሪክ፤ ሐተታ በሥርግው ገላው፤ አዲስ አበባ፡፡
More inside the PDF
Published
2018-01-01
How to Cite
አሰፋ, ታዬ. የሰብአዊነት አሣሣል በዐፄ ሱስንዮስ ዜና መዋዕል እና በበዓሉ ግርማ የቀይ ኮከብ ጥሪ ውስጥ. Ethiopian Journal of Languages and Literature, [S.l.], v. 14, n. 1, p. 1 - 32, jan. 2018. Available at: <http://ejol.aau.edu.et/index.php/EJOLL/article/view/2007>. Date accessed: 29 oct. 2020.
Please advise your journal citation style before using the above citation format, you can also find your citation style from citation formats listed down.