የሸንበተ ቆጮ ክዋኔ በሸካቾ ብሔረሰብ

Authors

  • Girum Areda PhD Candidate, AAU
  • Alemu Kasaye Addis Ababa University
  • Yenealem Aredo Addis Ababa University

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የሸንበተ ቆጮ ሀገረሰባዊ እምነት ክዋኔን መተንተን ነው። ጥናቱ በሸካቾ ዞን አንድራቻ እና ማሻ ወረዳዎች በሚገኙ ስምንት ቀበሌዎች ላይ ያተኮረ ነው። ጥናቱ ዓይነታዊ ገላጭ (Qualitative Descriptive) የምርምር ስልትን የተከተለ ሲሆን ምልከታ፣ ቃለ መጠይቅ እና የቡድን ውይይት የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎችን ተግባራዊ አድርጓል። የተሰበሰቡ መረጃዎችን ትርጉም ለመፈከር የክዋኔ መርና የትዕምርት ንድፈ ሀሳቦች ጥቅም ላይ ውለዋል። በጥናቱም የሸንበተ ቆጮ ክዋኔ የተፈጸመበት መቼት፣ የክዋኔውን ሂደት፣ የከዋኞቹን የአከዋወን ስልት፣ ክዋኔውን ይመለከቱ የነበሩ ተሳታፊዎች ለክዋኔው የነበራቸውን ስሜት እንዲሁም የድርጊቶችና የቁሶች ውክልና ተተንትነዋል። የሸንበተ ቆጮ ሀገረሰባዊ እምነት ክዋኔ ለአባታዊ ሙት አማልክት መንፈስ የሚቀርብ የመስዋዕት ሥርዓተ ክዋኔ ነው። የሸካቾ አባወራ ካመረተው ምርት ላይ ምንም ሳይነካ፣ ለቤት ፍጆታ ቀድሞ ሳያውል፣ ሳይሸጥና ሳይለውጥ ለአባታዊ ሙት አማልክት መንፈስ መስዋዕት ያቀርባል። በምላሹ ደግሞ የአባታዊ ሙት አማልክት መንፈስ የተመረተውን ምርትና ህይወታቸውን እንደሚባርክ፣ ከፈጣሪ (ከየሮቺ) ጋር እንደሚያስታርቅ፣ በራዕይ ወይም በመንፈስ ተገልጦ ምድራዊ ቤተሰቦቹን እንደሚመክርና እና እንደሚገስጽ፣ የሚያጋጥሟቸውን የህይወት ውጣ ውረዶች እና ውጥረቶች መቋቋም እንዲችሉ ያግዛል ተብሎ በብሔረሰቡ ዘንድ እንደሚታመን በጥናቱ ተመላክቷል።

Downloads

Published

2021-01-22