አጠቃላይ የጽሕፈት ሥርዓትና የፊደል ዳሰሳ ትኩረት በኢትዮጵያ የፊደል ገበታ ላይ (Ethiopic Script)

  • ተሾመ የኋላሸት (ዶ/ር)

Abstract

የጽሕፈት ሥርዓት መቼ እንደተጀመረ እና የት እንደተጀመረ በትክክል ባይታወቅም፤በጥንት ሰዎች የተሣሉ የዋሻ ውስጥ ሥዕሎች ለጽሕፈት መገኘት ምንጭ ናቸው ተብሎ ይገመታል፡፡ ለምሳሌ በሰሜን ስፔን አልታሚራ በሚባል ዋሻ ውስጥ የሚታዩ ሥዕሎችከዛሬ ሃያ ሺህ ዓመት በፊት በጥንታዊ ሰዎች እንደተሣሉና ዛሬም ድረስ እንደሚነበቡ ይነገራል፡፡ እነዚህ ሥዕሎችበወቅቱ የነበረውን የሕይወት ገፅታ የሚያሳዩ እንደሆኑም ይገመታል፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ሥዕሎች ለምን ጉዳይ እንደተሣሉ የሚታወቅበት ዘዴም ሆነ መንገድ የለም፤ ምናልባትም ከመግባቢያ መሳሪያነት ይልቅ ለሥነ ውበት መግለጫ የተሣሉ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለ፡፡(Fromkin & Rodman 1993፡364)፡፡


ለዚህ ጥናታዊ ጽሑፍ መነሻ ምክንያት የሆነው ነገር በአሁኑ ጊዜ አገራችን ውስጥ ስለፊደል የተለያዩና አንዳንዴም ኢ-ስነልሳናዊ  የሆኑ አመለካከቶች በስፋት ሲያንጸባርቁ ይስተዋላል፡፡ ለምሳሌ አንዳድ ሰዎች ይሄ ፊደል የኛን ቋንቋ ሊጽፍ አይችልም፤ ምክንያቱም አያጠብቅም፤ አያላላም፤ ድምጸትን አያመለክትም[1] ወዘተ. ያኛው ፊደል ግን የኛን ቋንቋ ሊጽፍ  ይችላል፤ ምክንያቱም ያጠብቃል ያላላል  ወዘተ. በማለት ሲከራከሩ ይሰማል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንድ ሰዎች የላቲን ፊደል ለኩሽና ለኦሞ ቋንቋዎች ብቻ፤ የኢትዮጵያው ፊደል ደግሞ ለሴም ቋንቋዎች ብቻ ተሰማሚና ምቹ ፈደሎች ናቸው ይላሉ፡፡ በመሰረቱ ማንኛውንም ቋንቋ በማንውም ፊደል መጻፍ ይቻላል[2]፡፡ ትልቁ ጉዳይ በአንጻራዊ መልኩም ቢሆን የትኛው ፊደል ለመማር ማስተማር ሂደት አስቸጋሪ ወይም ቀላል ነው የሚለው ሃሳብ ነው፡፡ እዚህ ላይ ልናስተውል የሚገባን ነገር፤ ሁሉም የጽሕፈት ሥርዓቶች ደካማና ጠንካራ ጎን እንዳላቸው ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ በተለይ በአሁኑ ዘመን እየተሠራባቸው ባሉት ሦስቱ የጽሕፈት ሥርዓቶች (ቃላዊ፤ ቀለማዊና ንጥረድምጻዊ) መካከል ስላለው ችግር እና ጠቀሜታ ጠቅለል ባለና ንፅፅራዊ በሆነ መልኩ ለመዳሰስ ይሞከራል፡፡ በተለይም በኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት በሥራ ላይ የዋሉትን የኢትዮጵያ የጽሕፈት ሥርዓትና የላቲን የጽሕፈት ሥርዓትን ዘርዘር ባለ መልኩ ለማቅረብ ይሞከራል፡፡ ጠንካራና ደካማ ጎናቸው ላይም ጥናቱ ጥቆማ ያደርጋል፡፡


 

References

Charles Ferguson 1976. “The Ethiopian Language Area.” in Bender, et.al. Languagein Ethiopia. (PP 63-76) London: Oxford University Press.
Fromkin V. & Rodman R. 1993, An Introduction to Language. Harcourt Brace Jovanovich College Publishers.
Gelb, I. J. 1952. A study of writing. University of Chicago Press. P. 27.
ሙሉጌታ ስዩም 2007. የኢትዮጵያ ፊደል ለኢትዮጵያ ቋንቋዎች፡፡ ያልታተመ፡፡
ባዬ ይማምና ቲም ’89 1989. ‹‹ፊደል እንደገና፡፡›› የኢትዮጵያ የቋንቋዎችና የሥነ-ጽሑፍ መጽሔት ቁጥር 7 (ገጽ 1-32) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ፡፡ አዲስ አበባ
ባዬ ይማም 1984. ‹‹ስርዓተ ጽሕፈት፡፡››ውይይት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህብር መጽሔት፡፡3ኛ ሴሪ፤ ቅጽ 1 ቁጥር 1 (ገጽ 17-41). አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ፡፡ አዲስ አበባ
አስረስ የኔሰው 1951.የካም መታሰቢያ የኢትዮጵያ ፊደል መሠረትነት መታወቂያ፡፡ አስመራ ኮከበ ጽባሕ ማተሚያ ቤት ዘማኅበረ ሐዋርያት ፍሬ ሃይማኖት፡፡
Published
2017-01-08
How to Cite
የኋላሸት (ዶ/ር), ተሾመ. አጠቃላይ የጽሕፈት ሥርዓትና የፊደል ዳሰሳ ትኩረት በኢትዮጵያ የፊደል ገበታ ላይ (Ethiopic Script). ZENA - LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures), [S.l.], v. 26, n. 1, p. 97 - 118, jan. 2017. ISSN 2222-6028. Available at: <http://ejol.aau.edu.et/index.php/AELC/article/view/1157>. Date accessed: 20 aug. 2019.
Please advise your journal citation style before using the above citation format, you can also find your citation style from citation formats listed down.