የዓለምን ከንቱነት የሚሰብኩ የዐማርኛ ቃለ ግጥሞች

  • መስፍን መሰለ

Abstract

አኅጽሮተ ጥናት


          የዓለምን ከንቱነት የሚሰብኩ የዐማርኛ ቃለ ግጥሞች፣  ዘገየም ፈጠነ ሞት የኹሉም ሰው ዕጣ ፈንታ መኾኑን ይሰብካሉ፡፡ ከሞት በኋላም ሰው ዘለዓለማዊ ሕይወትን ይወርስ ዘንድ በሕይወተ ሥጋ እያለ ለሕይወተ ነፍስ እንዲተጋ ያሳስባሉ፡፡ በክርስትና እምነት የነፍስ ከሥጋ መለየት የመጀመሪያ ሞት ነው፡፡ ይኽ ዓይነቱ ሞትም እንደ ማንቀላፋት ይቆጠራል፡፡ ከሥጋ ሞት በኋላ ትንሣኤ ስላለ ሰው በሥጋው ሲሞት ነፍሱ ከሥጋው ተለይታ ወደ እግዚአብሔር ትመለሳለች፣ ፍርድንም ትቀበላለች፡፡ በመኾኑም፣ ሰው ሞተ ነፍስ እንዳይደርስበት ሃይማኖታዊ ሕግን በማክበር፣ በእምነት በመኖር፣ ምጽዋት በመስጠት፣ ፈቃደ ሥጋን በመተው ከኹለተኛ ሞት እንደሚድን ቃለ ግጥሞቹ ይሰብካሉ፡፡ እንዲኽ ዓይነት መልእክት የሚተላለፍባቸው ቃለ ግጥሞች በደስታና በኀዘን አጋጣሚዎች በልዩ ልዩ መንገድ ይቀርባሉ፡፡


          ይኽን ጥናት ማካኼድ ያስፈለገበት ምክንያት፣ በተጠቀሱት መልእክቶች ላይ ትኩረት በሚያደርጉ የዐማርኛ ቃለ ግጥሞች ላይ የተደረገ ጥናት አለመኖርና ክፍተቱን ለማጥበብ ምርምር ማድረግ አስፈላጊ በመኾኑ ነው፡፡ የጥናቱ ዐቢይ ዓላማ የዓለመ ሕይወትን ከንቱነት የሚሰብኩ የዐማርኛ ቃለ ግጥሞችን መመርመር ነው፡፡ ከዚኽ የሚመነጩ ዝርዝር ዓላማዎችም፡- የሞትን አይቀሬነትና የሀብተ ሥጋን ቀሪነት የሚያስገነዝቡ፣ ከሞተ ነፍስ ለመዳን መመነንን የሚያበረታቱ፣ ሃይማኖታዊ ምግባር መፈጸም አስፈላጊ መኾኑን የሚሰብኩ ቃለ ግጥሞችን መመርመር የሚሉት ናቸው፡፡ ይኽ ጥናት ኅብረተ ሰቡ ስለ ሕይወተ ሥጋና ሕይወተ ነፍስ ያለውን ግንዛቤ በአጠቃላይ ንጽረተ ዓለሙንና የንጽረተ ዓለሙን መነሻ ምክንያቶች፣ እንዲሁም፣ በኅብረተ ሰቡ የዕለት ተለት ሕይወት ላይ ያላቸውን ተፅዕኖ ለመረዳት የሚጠቅም ከመኾኑም ባሻገር ወደ ፊት ለሚደረጉ ተመሳሳይ ጥናቶች እንደ መነሻ ሊያገለግል ይችላል፡፡ ለጥናቱ የሚያስፈልጉ መረጃዎች የተሰበሰቡት ከተለያዩ ጽሑፎችና ከሀገር ሽማግሌዎች ነው፡፡ ቃለ ግጥሞቹ ለትንተና የተመረጡት ዓላማ ተኮር ናሙናን (purposive sampling) መሠረት በማድረግ ነው፡፡  

References

ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል፡፡ ፲፱፻፷፩፡፡ ዝክረ ነገር፡፡ አዲስ አበባ፤ ሴንተራል ማተሚያ ቤት፡፡
ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል፡፡ ፲፱፻፺፱፡፡ አማርኛ ቅኔ ከነመፍቻው ፡፡ (፪ኛ ዕትም) አዲስ አበባ፤ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፡፡
ምስጋናው ታደሰ፡፡ 2008፡፡ ሚካኤል ንጉሠ ወሎ ወትግሬ፡፡ አደስ አበባ (ማተሚያ ቤቱ አልተገለጸም)፡፡
ሰይፉ መታፊሪያ፡፡ 1993 (እ.ኤ.አ)፡፡ “የፎክሎር መዝገበ ቃላት ጥንቀራ ቅድመ-ዝግጅት”፡፡ የኢትዮጵያ ጥናት መጽሔት JOURNAL OF ETHIOPIAN STUDIES. Vol. XXVI, No. 1, pp. 73 - 116.
ሥርገው ሐብለ ስላሴ፡፡ ዳግማዊ ምኒልክ የአዲሱ ሥልጣኔ መሥራች፡፡ (ዓመተ ምሕረቱ፣ የታተመበት ቦታና አሳታሚው አልተገለጹም፡፡
ሥርግው ገላው (ሐተታ)፡፡ 2002፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ [ተክለ ኢየሱስ እንደጻፈው]፡፡ አዲስ አበባ፤ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፡፡
ባሕሩ ዘውዴ፡፡ 2008፡፡ ሀብቴ አባ መላ፤ ከጦር ምርኰኛነት እስከ አገር መሪነት፡፡ አዲስ አበባ፤ ኢክሊፕስ ማተሚያ ቤት፡፡
ባሕሩ ዘውዴ፡፡ 1999፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1847 እስከ 1983፡፡ አዲስ አበባ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ፡፡
ተሰማ ሀብተ ሚካኤል ግጽው፡፡ ፲፱፻፶፩፡፡ ከሣቴ ብርሃንና ተሰማ የዐማርኛ መዝገበ ቃላት፡፡ አዲስ አበባ፤ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፡፡
More inside the PDF
Published
2017-01-08
How to Cite
መሰለ, መስፍን. የዓለምን ከንቱነት የሚሰብኩ የዐማርኛ ቃለ ግጥሞች. ZENA - LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures), [S.l.], v. 26, n. 1, p. 52 - 96, jan. 2017. ISSN 2222-6028. Available at: <http://ejol.aau.edu.et/index.php/AELC/article/view/1156>. Date accessed: 20 oct. 2019.
Please advise your journal citation style before using the above citation format, you can also find your citation style from citation formats listed down.