የጠበል ፎክሎራዊ ገጽታ በጨፋ/በጎንዴ ጠበል ማሳያነት

  • ፍሬህይወት ባዩ

Abstract

አጠቃሎ


ይህ ጥናት ያተኮረው በጨፋ ጠበል ፎክሎራዊ ክዋኔ ላይ ነው። በተለምዶ ጠበሉ የፈለቀበት አካባቢ በሚጠራበት ስም የጨፋ/የጎንዴ ጠበል በመባል ይታወቃል። በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን ሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ይገኛል። ጥናቱ የፎክሎርን የጥናት መስክ መሠረት አድርጎ ከ2005 እስከ 2008 ዓ.ም ድረስ በተለያየ ጊዜ በቃለ-መጠይቅና በምልከታ በተገኘ መረጃ ላይ ተመሥርቶ የተከናወነ ነው። የጠበሉ መፍለቅ ለጨፋ መድሀኒዓለም ደብረቁስቋም፣ ቅድስት ማርያም ወሰሎሜ አንድነት ገዳም መመሥረት ምክንያት ሆኗል። በጠበሉ የሚገለገሉት የእስልምናና የኢ.ኦ.ተ.ቤ ሃይማኖት ተከታዮች ሲሆኑ ጠበል ለመነከርና ለመጠጣት የሚመጡት የጤና መታወክ የደረሰባቸው ግለሰቦች ናቸው። የውሀ ምንጩ ከተራ ውሃነት ወደ ተቀደሰ ውሃነት የተቀየረው በራእይ አማካይነት ነው። ራእይ አንዱ የሚት ጥናት ትኩረት ነው። ከራእዩ ተረኩ ተገነባ። ተረኩ እምነትን መሠረተ። ራእዩ ሁለት ቤተ-ክርስቲያን ተሰርቶ ገዳም እንዲገደም ምክንያት ሆነ። ይህ ራእይ እንዲሁም ትረካ ለአማኙ ማህበረሰብ የተቀደሰ ትረካ ይሆናል። ለማያምንበት ደግሞ እንደ አተያዩ የተለያየ ትርጉም ወይም ሀቲት ሊሰጠው ይችላል። ትረካው በቃል ከአንዱ ወደ ሌላው እየተላለፈ እምነቱ እየሰፋ የጠበል ተጠማቂው ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ከሀያ ሶስት አመት በላይ ሆኖታል። ተጠማቂዎቹ ለጠበል አጠማመቁ በልማድ ብቻ ደንብ አውጥተውለታል። እያንዳንዱ የጠበሉ ተጠማቂ ስለ ጠበሉ በተለይ ከህመሙ ስለማዳኑ የሚተርካቸው ግለ ታሪኩ “ጠበል ያድናል” የሚለውን እምነት የሚተክሉ ናቸው። በጥቅሉ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ በጠበል ምክንያት የተገናኙ ማህበረሰቦች እምነት፣ አተያይ፣ ሃይማኖት ያልገደበው ማህበራዊ መስተጋብር  የሚታይበት ነው።  

References

Dundes, A. 1965.The study of Folklore, Prentice-Hall, Inc, ENgle wood, cliffs, N.J.
__________ 1976. Projection in Folklore: A Plea for Psychoanalytic Semiotics. Modern Language Notes 91:1500–1533.
Fennegan, R. 1992. Oral tradition and verbal arts, International Thomson publishing Company. London.
Kalkelachew Ali. 1997. “Religion, Rituals and Mutual Tolerance in Wollo,” M.A. Thesis, Department of Sociology and Social Anthropology, Addis Ababa University.
Kothari, C.R. 2004. Research Methodology, New age international publishers, Newil. New York.
Segal A. 2004. Very short Introductions; oxfored university press.
ማዕከላዊ እስታስቲክስ ኤጀንሲ። 2002። የ1999ዓ.ም የኢትዮጵያ ህዝብና ቤት ቆጠራ፤ ዐዲስ አበባ።
ወርቁ ከተማ። 2000። “የሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ፣ የጨፋ መድኃኒዓለም፣ ደብረ ቁስቋም፣ቅድስትማርያምና ቅድስት ሰሎሜ የሴቶች አንድነት ገዳም፣ አመሠራረት ፎክሎራዊ ገጽታ።” ሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ፣ ኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነጽሁፍ ትምህርት ክፍል፤ የኢትዮጵያ ስነጽሁፍና ፎክሎር የድህረ ምረቃ ፕሮግራም፣ ዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ።
የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዴሚ። 2006። የአማርኛ መዝገበ ቃላት። ዐዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ማተሚያ ቤት። ዐዲስ አበባ።
የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን። 1988። መርሐጽድቅ ባህለ ሃይማኖት። ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት። ዐዲስ አበባ።
ደስታ ተክለ ወልድ። 1962። ዐዲስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት፤ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት። ዐዲስ አበባ።
Published
2017-01-08
How to Cite
ባዩ, ፍሬህይወት. የጠበል ፎክሎራዊ ገጽታ በጨፋ/በጎንዴ ጠበል ማሳያነት. ZENA - LISSAN (Journal of Academy of Ethiopian Languages and Cultures), [S.l.], v. 26, n. 1, p. 1 - 18, jan. 2017. ISSN 2222-6028. Available at: <http://ejol.aau.edu.et/index.php/AELC/article/view/1154>. Date accessed: 19 july 2019.
Please advise your journal citation style before using the above citation format, you can also find your citation style from citation formats listed down.